የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሠራተኛ ደንብ ልብስ ድጋሚ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሠራተኛ ደንብ ልብስ NCB 0012/2017 ድጋሚ
ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር NCB-0012/2017
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሠራተኛ ደንብ ልብስ ድጋሚ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበት መረጃ፣ በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የቲን ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት እና የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃዎች ያሏቸው ለመሆኑ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ቢድ ቦንድ ብር 10,000.00 በባንክ በተመሰከረለት ቼክ፣ ወይም በባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስም ሞልተው ከኦሪጅናል ቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዋጋና የቴክኒክ መግለጫዎች አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግና የጨረታውን ስምና ቁጥር በመጥቀስ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ሸጎሌ ጊቢ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡30 ተዘግቶ ከጠዋቱ 5፡45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ሸጎሌ ጊቢ ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0115172521 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
