ድርጅታችን በላይአብ ኬብል አምራች ኃ/የተ/የግ/ማ የፋብሪካ የፒቪሲ ተረፈ ምርት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን በላይአብ ኬብል አምራች ኃ/የተ/የግ/ማ የፋብሪካ የፒቪሲ ተረፈ ምርት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ከታች የቀረበውን ዝርዝር መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
|
1 |
ፒቪሲ ስክራፕ (PVC insulation Scrap) |
በኪ.ግ |
6,329.40 |
- ተጫራቶች ጨረታው በዚህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት በመቅረብ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ዕቃውን ለማየት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ባሉት የስራ ሰዓት በድርጅቱ ፋብሪካ አዳማ ወንጂ ማዞሪያ ቀበሌ 09 በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዋና መ/ቤት አዲስ አበባ ወይም ፋብሪካ አዳማ በመቅረብ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው የስራ ቀን እና የጨረታ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት 16ኛው ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት አዲስ አበባ ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ለቡ ኢንዱስትሪ መንደር በአካል በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቶች የሚያቀርቡትን ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በድርጅቱ ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያው ዋስትና ለአሸናፊዎች ሙሉ ክፍያውን እንደከፈሉና ማስረጃ እንዳቀረቡ የሚለቀቅ ሲሆን ለተሸናፊዎች ግን የጨረታ ውጤቱ እንደፀደቀ ይሆናል።
- አሸናፊ ተጫራች ከድርጅቱ ጋር የሽያጭ ውል ስምምነት ይፈራረማል ከተፈራረመ በኃላ የሚጠበቅበትን ክፍያ በማጠናቀቅ ዕቃውን ይረከባል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ስለ ጨረታው ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114711014/ 0966215515 ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በላይአብ ኬብል አምራች ኃ/የተ/ግ/ማ
