የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ሳሪስ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ መለያ ቁጥር 02/2017 አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ሳሪስ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ መለያ ቁጥር 02/2017 አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 - የሰራተኛ ደንብ ልብስ፣
- ሎት 2 - የጽዳት እቃዎች፣
- ሎት 3 - የተለያዩ መድሃኒት፣
- ሎት 4 - የተለያዩ ሪኤጀንት
ከላይ የተዘረዘሩት እቃዎች ላይ መጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች:-
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ያላቸው፤ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤ ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት እነዚህን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ከሳሪስ ጤና ጣቢያ ከፋ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 35 የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ሎት 1 (ደንብ ልብስ) 31,600.00 (ሰላሳ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ብር) ፣ ሎት 2 (የጽዳት እቃዎች) 15,300.00 (አስራ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ብር) ፣ ሎት 3 (የተለያዩ መድሃኒቶች) 32,950.00 (ሰላሳ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ብር) ፣ ሎት 4 (የተለያዩ ሪኤጀንት) 40,580.00 (አርባ ሺህ አምስት መቶ ሰማንያ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በአድራሻችን ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ተወዳድረው አሸናፊ ከሆኑ የአሸነፈው ድርጅት የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ 10% ለሥራ አፈፃጸም ዋስትና በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዛኑ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸቸው ባሉበት ሳሪስ ጤና ጣቢያ ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 35 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታ ሂደት በተቀመጠው መስረት ይካሄዳል፡፡ የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከመስሪያ ቤቱ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ የዋጋ ዝርዝር ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩት እቃዎች ሣምፕል ሙሉ በሙሉ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሙሉ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመለየት የመስሪያ ቤታችሁን ማህተም በማድረግ እና በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ፊርማችሁን በመፈረም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ካደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ሲኖራቸው የጨረታ ሰነድ በነጻ ይወስዳሉ፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሎ ስርዝ ድልዝ ካለው የተሠረዘው እቃ ከጨረታ ውጪ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ መስሪያ ቤቱ ባወጣው እስፔክ መሠረት ብቻ ነው፤ እስፔኩን በራሳቸው የቀየሩት እቃ ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ቫትን አካቶ መሆን አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ሳሪስ 3F ፊት ለፊት ከሙኒክ ሆቴል አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡- 011-4-70-98-59/011-4-70-79-77
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የሳሪስ ጤና ጣቢያ
