በሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የዘመናዊ የህንጻ ኢንዱስትሪዎች ኃ/የተ/የግል ማህበር ለተለያዩ የምርት ግብዓት የሚሆኑ የተለያዩ የማዕድን ጥሬ እቃዎችን፣ የሰራተኛ የደንብ አልባሳትን፣ የLCD Vidio display & Digital LED Advertising እና የቀለም ማሸጊያ የፕላስቲክ ባልዲ (Plastic pail) ባለ16 ሊተር እና ባለ 35 ሊትር ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዘ.ህ.አ/05/2017
በሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የዘመናዊ የህንጻ ኢንዱስትሪዎች ኃ/የተ/የግል ማህበር ለተለያዩ የምርት ግብዓት የሚሆኑ የተለያዩ የማዕድን ጥሬ እቃዎችን፣ የሰራተኛ የደንብ አልባሳትን፣ የLCD Vidio display & Digital LED Advertising እና የቀለም ማሸጊያ የፕላስቲክ ባልዲ (Plastic pail) ባለ16 ሊተር እና ባለ 35 ሊትር ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም:-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ ንግድ ፈቃድ ሰርተፊኬት፣ የንግድ ምዝገባ ሠርተፊኬት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት፤ እንዲሁም የቲን ሰርተፊኬት ማቅረብ
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የመጫረቻ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከወጣበት ቀን አንስቶ በተከታታይ ባሉት 10 /አስር/ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ሜክሲኮ ጠማማ ህንፃ ወረድ ብሎ በሚገኘው አዲስ ጋዝ ግቢ ሽያጭ ቢሮ ወይም ከሸገር ገላን ከተማ ወደ ዱከም በሚወስደው መንገድ ከሰንሻይን ኮንስትራክሽን አለፍ ብሎ በሚገኘው ድርጅታችን ግዥ ክፍል ውስጥ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በታወቁ ባንኮች በተረጋገጠ ሲፒኦ ከዚህ በታች ለቀረቡ ጥቅሎች (ሎት) ለእያንዳንዳቸው በተናጠል ማቅረብ አለባቸው።
ለሎት 1 ለተለያዩ የማዕድን ጥሬ እቃዎች ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ብቻ
ለሎት 2 ለሰራተኛ የድንብ አልባሳትን፣ 10.000 (አስር ሺህ ብር) ብቻ።
ለሎት 3 ለLCD Vidio display & Digital LED Advertising 10,000 (አስር ሺህ ብር) ብቻ
ለሎት 4 ለቀለም ማሸጊያ የፕላስቲክ ባልዲ ባለ 3.5 ሌትር እና 16 ሊትር (Plastic pail) 10,000 (አስር ሺህ ብር) ብቻ
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታው አየር ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ አስረኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ገላን በሚገኘው ድርጅታችን ግዥ ክፍል ውስጥ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ11 (አስራ አንደኛው) የስራ ቀን ቅዳሜን ጨምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ገላን በሚገኘው ድርጅታችን ግዥ ክፍል ውስጥ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን እቃዎች እስከ ድርጅቱ የመረከቢያ ቦታ በራሳቸው ትራንስፖርት ያጓጉዛሉ፣ የገጠማ ስራዎችን በራሳቸው ወጪ ይሸፍናሉ፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የውል ስምምነት በሚፈፅምበት ጊዜ የውሉን አጠቃላይ ገንዘብ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በሲፒኦ በሁኔታ ያልተገደበ የባንክ ዋስትና ያቀረባል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
ዘመናዊ ህንፃ ኢንዳስትሪ ኃሳ/የተ/የግ/ማህበር
ገላን ከተማ
ስልክ ቁጥር +251 911224546/+251 911548320
በሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ
የዘመናዊ የህንጻ ኢንዱስትሪዎች ኃ/የተ/የግል ማህበር
