የቤኒሻንጉል ክ/መ/ፋይናንስ ቢሮ ለ2017 ዓ.ም ሊገዛቸው ካቀዳቸው ግዥዎች ውስጥ አንዱ የሰራተኛ ደንብ ልብስ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የግዥ ጨረታ
ጽ/ቤታችን 2017 ዓ.ም ሊገዛቸው ካቀዳቸው ግዥዎች ውስጥ አንዱ የሰራተኛ ደንብ ልብስ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በዘርፉ ሥራ ለተሰማሩ ድርጅቶች የሚከተለውን መስፈርቶች ለሚያሟሉ ድርጅቶች ጨረታውን በጋዜጣ እንዲያወጡልን የተለመደውን ትብብራችሁን እየጠየቅን የጨረታው መስፈርት ከዚህ በታች እንደሚከተሉት ናቸው።
- የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት (አስራ አምስት ቀን) በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ተኛው (በአስራ ስድስተኛው ቀን) ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቤ/ጉ/ክ/መ/ገ/ኢ/ል/ቢሮ ቁጥር-1 ይከፈታል ቀኑ የሥራ ቀን ከሆነ ወይም ህዝባዊ በዓላቶች እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን እንዲከፈት ይደረጋል።
- ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት በራሳቸው ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው ተገኝተው የጨረታ ሂደቱን መከታተል ይችላሉ።
- ተወዳዳሪዎቹ የቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ የተሟላ እስከሆነ ድረስ ባለመገኘቱ ምክንያት ከውድድር ውጪ አይደረግም።
የተወዳዳሪዎች መስፈርት
- ህጋዊ የሆነ ሥራ ፈቃድ ያለው/ያላት ሆኖ በ2017 በጀት ዓመት ያሳደሱ
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከቤ/ጉ/ክ/መ/አሶሳ ዞን/ገ/ኢ/ል/መምሪያ ቁጥር 2 የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ብቻ ከፍለው መውሰድ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የዋጋው 2% ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በባንክ በተረጋገጠ CPO ገቢ ማድረግ አለባቸው።
- ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ሰነዱን ሞልተው ሲያቀርቡ ለቴክኒካል 1 ኦርጅናል 1 ኮፒ ሲሆን ለፋይናንሻል ደግሞ 1 ኦርጅናል እና 1 ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ አለበት፤
- ለአሸናፊ ድርጅቶች ክፍያ የሚፈፀመው ውል ለተገባባቸው ዕቃዎች ከቤ/ጉ/ክ/መ/ገ/ኢ/ል/ቢሮ አሶሳ ከተማ ላይ ሲያስረክብ መሆኑን እና ክፍያውን ጽ/ቤታችን በሚወክለው ሰራተኛ የሚከፈል ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0940749780 ደውሎ መረዳት ይቻላል።
የቤኒሻንጉል ክ/መ/ፋይናንስ ቢሮ
