Tender Detail

Tender Details


የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትም/ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በWFP/Word Food Program/ በዩኒሴፍ እና መደበኛ በጀት በመጠቀም፤ ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን ነገሮች በመስኩ የተሰማሩ የንግድ ድርጅቶች በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታቂያ

ጨረታ ቁጥር 09

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትም/ቢሮ 2017 በጀት ዓመት WFP/Word Food Program/ በዩኒሴፍ እና መደበኛ በጀት በመጠቀም፤

  1. የሞተር ሳይክል ግዥ
  2. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ግዥ
  3. በሞዳሊቲ-2 ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 3 የተፋጠነ ትምህርት የመማሪያና ማስተማሪያ መጻህፍት ህትመት
  4. የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የስነ-ተዋልዶ ጤና የህይወት ክህሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ህትመት
  5. በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚፈፀሙ ጾታዊ ጥቃት ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት የተዘጋጀ መመሪያ ህትመት
  6. ብሮሸር (Brochures and Leaflets) Amharic ህትመት
  7. ለአንደኛ ደረጃ ሴት ተማሪዎች ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ግዥ
  8. የፕሪንተር ቀለም ግዥ በመስኩ የተሰማሩ የንግድ ድርጅቶችን ለማወዳደር መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃዳቸውንና የምዝገባ ሰርተፊኬታቸውን ያሳደሱ በግብር ከፋይነት ተመዝግቦ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለውና የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን የምዝገባ ወረቀት፣ የዘመኑን የግብር ግዴታውን የተወጣ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበበት/መረጃ ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
  2. ተጫራቾች ትምህርት ቢሮ ቁጥር 18 በመቅረብ ለሥራው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከተራ ቁጥር 4-6 በጥቅሉ እና 7 ያሉትን ብር 300 በመክፈል መግዛት የምትችሉ ሲሆን ሌሎች የተቀሩትን ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
  3. የፋይናንሻል ሰነዳቸውን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ሰነድ ለየብቻ አሽጎ በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን በቢሮ ቁጥር 18 ለዚህ በተዘጋጀ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. ለተራ ቁጥር 1 2 እና 8 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ የሚገልጽ የገንዘብ መጠን ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው።
  5. በሞዳሊቲ-2 ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 3 የተፋጠነ ትምህርት የመማሪያና ማስተማሪያ መጻሕፍት ህትመት ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO ወይም የባንከ ጋራንቲ የሚገልጽ የገንዘብ መጠን ብር 35,000 /ሠላሣ አምስት ሺህ/ ብር የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው።
  6. ከተራ ቁጥር 4-6 በጥቅሉ እና 7 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ የሚገልጽ የገንዘብ መጠን ብር 10,000.00/አስር ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው።
  7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ 16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 600 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 830 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
  8. /ቤቱ በጨረታው ላይ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-046 775 2359/ 0916 863 055 መጠየቅ ይችላሉ።

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትም/ቢሮ

 

Save Tender