የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ከሚያርዳቸው እንስሳት የሚገኘውን የተለያዩ ተረፈ- ምርቶች ማለትም የዳልጋ ከብት የሽሆና ጅማት ፣ ቁርዝ ፣ ቀንድ ፣ ሀሞት ፣ የልብ ቧንቧ ፣ የግንባር ቆዳ ፣ ትንሹ አንጀት ፣ ቴስቲክል ፣ የሸሆና ጥፍር እና የበግና የፍየል አንጀት ፣ ቴስቲክል ፣ ቁርዝ ፣ የግመል ቆዳ ፣ እና ሌሎች በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፁ ተረፈ ምርቶችን ጨምሮ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የተለያዩ የእንስሳት ተረፈ ምርቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ከሚያርዳቸው እንስሳት የሚገኘውን የተለያዩ ተረፈ- ምርቶች ማለትም የዳልጋ ከብት የሽሆና ጅማት ፣ ቁርዝ ፣ ቀንድ ፣ ሀሞት ፣ የልብ ቧንቧ ፣ የግንባር ቆዳ ፣ ትንሹ አንጀት ፣ ቴስቲክል ፣ የሸሆና ጥፍር እና የበግና የፍየል አንጀት ፣ ቴስቲክል ፣ ቁርዝ ፣ የግመል ቆዳ ፣ እና ሌሎች በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፁ ተረፈ ምርቶችን ጨምሮ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች
- በመስኩ ወይም በተመሳሳይ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ የማይመለስ ኮፒ በማያያዝ ማቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በተጫራቾች መመሪያ ላይ በተገለፀው መሰረት ይሆናል፡፡
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መውሰድ ይቻላል፡፡
- የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘውን የጨረታ ሠነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገባት አለበት፡፡
- ጨረታው ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥር 0114-16-39-78 ደውለው መጠየቅ ይቻላል
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት