የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ የደንብ ልብስ ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ECWCT/NCB/PG-115/2017
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ የደንብ ልብስ ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ነገር ግን በአቅራቢዎች ዝርዝር ያልተመዘገቡ ተጫራቾች ለሚመለከተው የመንግስት መ/ቤት በማመልከት የምዝገባ ሰርተፍኬት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል የዘመኑ ግብር የከፈሉበት ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት፣ የአቅራቢነት ዝርዝር የምዝገባ ሰርተፍኬት እና በጨረታው ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢዎች ቢሮ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ በማቅረብ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የሃገር ውስጥ ጥቅል ግዥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡
- የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በአማረኛ ቋንቋ ነው።
- ተጫራቾች ለሚጫቱበት ጨረታ ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺ) በባንክ በተዘጋጀ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ግዥ መምሪያ-1 ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቀን ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት 8፡30 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቅጥር ግቢ በሚገኘው ግዥ መምሪያ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በግዥ መምሪያ ቢሮ
አድራሻ፡-ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህንፃ 200 ሜትር ገባ ብሎ አንድነት ኢንተርናሽናል ት/ቤት ፊት-ለፊት
ስልክ ቁጥር 011 8-96-29-91
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን
