የጥቁር አባይ ኮንስትራከሽን አ/ማህበር (ሕግ በመፍረስ ላይ ያለ) በአዲስ አበባ ሣሪስ ማዕከላዊ ጋራዥ ፣ ቃሊቲ ንብረት ማከማቻ መጋዘን እና አቃቂ ጠጠር ማምረቻ ግቢ ውስጥ የሚገኙትን ቀላል ተሽከርካሪዎች፣ መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የህክምና መገልገያ ዕቃዎች ፣ የቆርቆሮ መጋዘኖች እና ንቃይ ቆርቆሮዎች፣ ዛፎች እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ተሽከርካሪዎች ፣ የኮንስትራክሽን መሣሪያ መለዋወጫ እቃዎች ፣ የህክምና መገልገያ ዕቃዎች ፣ የቆርቆሮ መጋዘኖች እና ንቃይ ቆርቆሮዎች ፣ ዛፎች እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ ንብረቶች ፣ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ቁጥር 02/2017
የጥቁር አባይ ኮንስትራከሽን አ/ማህበር (ሕግ በመፍረስ ላይ ያለ) በአዲስ አበባ ሣሪስ ማዕከላዊ ጋራዥ ፣ ቃሊቲ ንብረት ማከማቻ መጋዘን እና አቃቂ ጠጠር ማምረቻ ግቢ ውስጥ የሚገኙትን ቀላል ተሽከርካሪዎች፣ መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የህክምና መገልገያ ዕቃዎች ፣ የቆርቆሮ መጋዘኖች እና ንቃይ ቆርቆሮዎች፣ ዛፎች እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) በመክፈል ሳሪስ ንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ አጠገብ ከሚገኘው ከማህበሩ ቢሮ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረቶች የጨረታ ሰነድ በመያዝ ዘወትር በሥራ ሰዓት የሚሰጠውን የመግቢያ ወረቀት በመያዝ ንብረቶቹ ባሉበት መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ (10%) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (ሲ ፒ.ኦ) በድርጅቱ ትክከለኛ ስም /BLUE NILE CONSTRUCTION SHARE COMPANY/ በማሰራትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በፖስታው ላይ የተጫራቹን ስምና አድራሻ በግልፅ በመፃፍ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- በቂ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ያላስያዙ ተጫራቾችን ኮሚቴው ከጨረታው ሊሰረዝ ይችላል።
- የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያው አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን የገዙበትን ዋጋ አጠቃለው ከከፈሉ በኋላ ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊዎች ውጤቱ በተገለፀ በ10 /አስር/ቀናት ውስጥ ክፍያ በመፈፀም ያሸነፉባቸውን ንብረቶች በ15 ቀናት ውስጥ አንስተው ማጠናቀቅ አለባቸው፤ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሳያነሱ ቢቀሩ ለሚፈጠረው ችግር መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
- ከላይ በተጠቀሰው 15 ቀናት ውስጥ ንብረቱን አጠናቆ ያልወሰደ (ያላነሳ) ተጫራች የመጋዘን ኪራይ በቀን ብር 100 (እንድ መቶ) እንዲከፍል ይደረጋል።
- አክሲዮን ማህበሩ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአ/ማህበሩ ቢሮ ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ በ4:30 ይከፈታል።
- ድርጅቱ ስለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 0114426332
የጥቁር አባይ ኮንስትራክሽን አ/ማህበር
