የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት የበቆሎ ፣ የስንዴና የገብስ ተረፈ ምርቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 007/ሽያጭ/17 ዓ/ም
የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት የበቆሎ ፣ የስንዴና የገብስ ተረፈ ምርቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- ተጫራቾች በሥራ ዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ /CPO/ በደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት ስም ከጨረታ ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ፤ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል በሀዋሳ ከተማ በሚገኘው በድርጅቱ የግዥ ፋይንናስ ንብረት አስተዳደር ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በማንኛውም በማይለቅ ማሸጊያ በታሸገ ፖስታ /ኤንቬሎፕ/ ውስጥ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒውን ከተጓዳኝ ማስረጃዎች ጋር በማደራጀት በድርጅቱ የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሳጥን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት በድርጅቱ የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 12 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ነገር ግን 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ፣ ሰዓትና ሁኔታ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን የተረፈ ምርት ዓይነቶችን የተከማቸበት መጋዘን በአካል በመቅረብ ናሙና በማየት በናሙናው መሠረት ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ሙሉ ስማቸውን፣ ፈርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ የጨረታ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ቀርቦ ቢገኝ ተጫራቹ ጨረታውን ከመሳተፍ ይታገዳል፡፡
- ድርጅቱ ለዚህ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 046 220 5992/09 38 07 78 32
የደቡብ ምርጥ ዘር ደርጅት
