የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ለድርጅቱ ሰራተኞች የሚሆን የደንብ ልብስ፣ ፍራሽ እና ሙሉ የዴኬር ዕቃዎች እና የህክምና ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ለድርጅቱ ሰራተኞች የሚሆን የደንብ ልብስ፣ ፍራሽ እና ሙሉ የዴኬር ዕቃዎች እና የህክምና ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
|
ተ/ቁ |
የግዥ ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ (ሰማያዊ ጨርቅ፤ ነጭ ሸሚዝ) |
20,000 |
|
ሎት 2 |
ፍራሽ እና ሙሉ የዴኬር ዕቃዎች |
20,000 |
|
ሎት 3 |
የህክምና ዕቃዎች |
10,000 |
- ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ ግብር የከፈሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እና ወቅታዊ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ቃሊቲ ማሰልጠኛ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ግዥ ክፍል በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከ8፡00 ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከተጠቀሰው ሰዓት ዘግይቶ የመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይሆናል፡፡
- የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡- +251-1-14-70-80-67
በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት
