የቢሾፍቱ አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች መስፈርቱን የሚያሟሉ በማይክሮ ኢንተርፕራይዝ (ኤጀንሲ) የተደራጁ ተጫራቾችን አወዳድሮ በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ቢሾፍቱ አጠቃላይ ሆስፒታል
- የአጠባ አገልግሎት (ላውንደሪ)
- የምግብ አቅርቦት
- የጥበቃ አገልግሎት
- የጽዳት አገልግሎት
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በማይክሮ ኢንተርፕራይዝ (ኤጀንሲ) የተደራጁ ተጫራቾችን አወዳድሮ በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በቅርብ/በ2017 የታደሰ ከስራው ጋር የተዛመደ የንግድ እና የሙያ ፈቃድ እንዲሁም Tin Number ያለው።
- ለአጠባ አገልግሎት፣ ለጽዳት አገልግሎትና ለጥበቃ አገልግሎት የሥራ ልምድ ያለው፤ በሦስቱም አገልግሎቶች ሠራተኞች/ሰነድ ላይ የተጠየቀውን የሰው መጠን ማቅረብ የሚችል፡፡
- በምግብ ዝግጅት እና መስተንግዶ የስራ ልምድ ያለው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ለማይክሮ 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ለኤጀንሲ 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በሆስፒታሉ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ ዋጋ ሳይሆን በጠቅላላ ዋጋ የተሻለ ካቀረቡ የሚያልፉ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የታሸገ ፖስታ ወይም ኤንቨሎፕ ሰነዶች ኦርጅናል እና ኮፒ የጨረታ ሰነዱ ላይ ያለውን መስፈርት አሟልቶ የተገኘና የኃላፊው ስምና ፊርማ ማህተም ያለው መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 47 በእያንዳንዱ ሎት
- ሎት 1 የአጠባ አገልግሎት (የላውንደሪ)
- ሎት 2 የምግብ አቅርቦት
- ሎት 3 የጥበቃ አገልግሎት
- ሎት 4 የጽዳት አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታውን የሚያልፍ ተወዳዳሪ በሆስፒታሉ ከሐምሌ 01/2017 - ሰኔ 30/2018 ዓ.ም አገልግሎቱን እየሰጠ የሚቆይ መሆኑን አውቆ ውል የሚፈርም መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናትና በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በአስራ አንደኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ ላይብረሪ ይከፈታል፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 0114371271/ 0114338187 መደወል ይችላሉ።
በኦሮሚያ ጤና ቢሮ የቢሾፍቱ አጠቃላይ ሆስፒታል
