ኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር በተሽከርካሪዎች ጥገና ወቅት የሚወገድ የተቃጠለ ዘይት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 010/2017
ኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር በተሽከርካሪዎች ጥገና ወቅት የሚወገድ የተቃጠለ ዘይት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ፤
- ደብረዘይት መንገድ ሳሪስ ከሚገኘው የድርጅቱ ሽያጭ ክፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሠነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 –10፡00 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
- ተጫራቾች የሚወገደውን የተቃጠለ ዘይት እስከ ጨረታው መዝጊያ ጊዜ በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00-10፡30 ድረስ በአክሲዮን ማህበሩ የተሽከርካሪ ጥገና ክፍል በአካል ተገኝተው ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሃምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ድርጅቱ ለጨረታ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO በማዘጋጀት ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ አካተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሃምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 440 1913 በመደወል መረዳት ይቻላል።
ኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር
