የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን የሆኑ ንብረቶች ብረታ ብረቶችን፤ አሮጌ ጎማዎች እና ባዶ በርሜሎችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡-ኢ/ኤ/አ/አ/ሪ/ብሔ/ግ/ጨ/-001/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን የሆኑ ንብረቶች ብረታ ብረቶችን፤ አሮጌ ጎማዎች እና ባዶ በርሜሎችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
ሎት |
የሚገኝበት ቦታ |
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) |
የጨረታው መዝጊያ ቀን |
የጨረታው መክፈቻ ቀን |
|
1 |
ብረቶች (ክሮስአርም፤ ታይ ስትራፕ፤ የድራም ብረቶች) |
ሎት-1 |
አምቦ ከተማ |
40,000.00 (አርባ ሺህ ብር ብቻ) |
ከሐምሌ 07 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ከሐምሌ 07 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
|
2 |
አሮጌ ጎማዎች |
|||||
|
3 |
ባዶ በርሜሎች |
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በድርጅታችን አካውንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር (1000254843017 EEU Ambo District Connection Fee) የማይመለስ ብር 600 /ስድስት መቶ ብር/ ገቢ በማድረግ ዘወትር በስራ ስዓት አምቦ ከተማ የዱሮ ሃዮሜ ኮሌጅ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 አምቦ ሪጅን የአቅርቦት ሰንሰለት እና ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ በመምጣት የሚወገዱትን ንብረቶች ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ገዝተው ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት፤ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን በሚገኙበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Security) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ስማቸውን እና ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/አ/ሪ/ብሔ/ግ/ጨ/-001/2018 በመግለፅ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት አምቦ ከተማ የዱሮ ሃዮሜ ኮለጅ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 አምቦ ሪጅን የአቅርቦት ሰንሰለት እና ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ በሚገኘው ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-2-60-97-77 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን
