Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፈዴሬሽን ኃላ/የተ/ አሰላ ብቅል ፋብሪካ
  • Address አዲስ አበባ ከተማ ከጀርመን አደባባይ ወደ ሚካኤል አደባባይ በሚወስደው መንገድ ላይ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፈዴሬሽን ሕንፃ ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ወይም አሰላ- ቁሉምሳ : ኢትዮጵያ, Phone: 09-65-65-04-81
  • Website
  • Deadline17 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2025-07-17 00:00:00
  • Categories Byproducts

በኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተወሰነ አሰላ ብቅል ፋብሪካ በጎተራ ተከማችቶ የሚገኘውን 3,000 /ሶስት ሺህ/ ኩንታል 3ኛ ደረጃ ብጣሪ ገብስ /ተረፈ ምርት/ ውል እንደተዋዋለ ሙሉ ክፍያውን በቅድሚያ ፈፅሞ በሃያ (20) ቀናት ውስጥ ሊያነሳ ለሚችል ገዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


 

3 ደረጃ ብጣሪ ገብስ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር OACF-AMF/MBSM/03/2017

 

በኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን /የተወሰነ አሰላ ብቅል ፋብሪካ በጎተራ ተከማችቶ የሚገኘውን 3,000 /ሶስት ሺህ/ ኩንታል 3 ደረጃ ብጣሪ ገብስ /ተረፈ ምርት/ ውል እንደተዋዋለ ሙሉ ክፍያውን በቅድሚያ ፈፅሞ በሃያ (20) ቀናት ውስጥ ሊያነሳ ለሚችል ገዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎትና አቅም ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

  1. ተጫራቾች 2017 . የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN No./ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. በእህል ንግድ ወይንም የከብቶች መኖ በማዘጋጀት ሕጋዊ የሆነ የንግድ ፍቃድ ያላቸው።
  3. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በፋብሪካችን አካውንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000257808697 ወይም በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ 1000043405229 በመክፈል/ገቢ በማድረግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት 200-600 ከሰዓት በኋላ 700-1000 ሰዓት ቅዳሜ ጠዋት 200- 6:00 ሰዓት ድረስ አሰላ-ቁሉምሳ በሚገኘው ፋብሪካችን ቢሮ ቁጥር 051 ወይንም አዲስ አበባ በሚገኘው ዋና /ቤት ከጀርመን አደባባይ ወደ ሚካኤል አደባባይ በሚወሰደው መንገድ ላይ ሚካኤል /ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ህንፃ 6 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) በባንክ በተመሰከረለት .. /C.P.O/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 10 ቀን 2017 . ከቀኑ 800 ሰዓት ድረስ በአየር ላይ ክፍት ሆኖ ይቆያል።
  6. ተጫራቾች በኤንቨሎፕ የታሸገ የጨረታ ሰነዳቸውን በአሰላ ብቅል ፋብሪካ ቢሮ ቁጥር 051 በተቀመጠው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  7. ጨረታው በዕለቱ ሐምሌ 10 ቀን 2017 . ከቀኑ 800 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 815 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አሰላ /ቁሉምሳ/ በሚገኘው የፋብሪካችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  8. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ ጨረታ ሰነዳቸውን የሚያቀርቡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
  9. ፋብሪካው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡- 022 331 5266 ወይም 022 331 8197 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

በኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን /የተወሰነ የአሰላ ብቅል ፋብሪካ

 

Save Tender