በኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተወሰነ አሰላ ብቅል ፋብሪካ በጎተራ ተከማችቶ የሚገኘውን 3,000 /ሶስት ሺህ/ ኩንታል 3ኛ ደረጃ ብጣሪ ገብስ /ተረፈ ምርት/ ውል እንደተዋዋለ ሙሉ ክፍያውን በቅድሚያ ፈፅሞ በሃያ (20) ቀናት ውስጥ ሊያነሳ ለሚችል ገዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የ3ኛ ደረጃ ብጣሪ ገብስ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር OACF-AMF/MBSM/03/2017
በኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተወሰነ አሰላ ብቅል ፋብሪካ በጎተራ ተከማችቶ የሚገኘውን 3,000 /ሶስት ሺህ/ ኩንታል 3ኛ ደረጃ ብጣሪ ገብስ /ተረፈ ምርት/ ውል እንደተዋዋለ ሙሉ ክፍያውን በቅድሚያ ፈፅሞ በሃያ (20) ቀናት ውስጥ ሊያነሳ ለሚችል ገዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎትና አቅም ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
- ተጫራቾች የ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN No./ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- በእህል ንግድ ወይንም የከብቶች መኖ በማዘጋጀት ሕጋዊ የሆነ የንግድ ፍቃድ ያላቸው።
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በፋብሪካችን አካውንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000257808697 ወይም በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ 1000043405229 በመክፈል/ገቢ በማድረግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት 2፡00-6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10፡00 ሰዓት ቅዳሜ ጠዋት 2፡00- 6:00 ሰዓት ድረስ አሰላ-ቁሉምሳ በሚገኘው ፋብሪካችን ቢሮ ቁጥር 051 ወይንም አዲስ አበባ በሚገኘው ዋና መ/ቤት ከጀርመን አደባባይ ወደ ሚካኤል አደባባይ በሚወሰደው መንገድ ላይ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ /C.P.O/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በአየር ላይ ክፍት ሆኖ ይቆያል።
- ተጫራቾች በኤንቨሎፕ የታሸገ የጨረታ ሰነዳቸውን በአሰላ ብቅል ፋብሪካ ቢሮ ቁጥር 051 በተቀመጠው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በዕለቱ ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ8፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አሰላ /ቁሉምሳ/ በሚገኘው የፋብሪካችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ ጨረታ ሰነዳቸውን የሚያቀርቡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- ፋብሪካው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡- 022 331 5266 ወይም 022 331 8197 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተወሰነ የአሰላ ብቅል ፋብሪካ
