በጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቅድ ማስፈፀሚያ የሚውሉ የተለያዩ የአገልግሎት ግዥ ፣ የደንብ ልብስ እና የአቃቤ ህግ የችሎት ልብስ ሱፍ ጨርቅ በገበር የተሰፋና የጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ግዥ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡-ጉ/ክ/ከ/ዋ/ስ/አስ/ፋ/ጽ/ቤት /ግዥ ቡድን 01/2017 ዓ.ም
በጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቅድ ማስፈፀሚያ የሚውሉ የተለያዩ የአገልግሎት ግዥ ፣ የደንብ ልብስ እና የአቃቤ ህግ የችሎት ልብስ ሱፍ ጨርቅ በገበር የተሰፋና የጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1. የተለያዩ የጉዞ መኪናዎች ኪራይ
- ሎት 2. የታሸገ ውሃ ግዥ
- ሎት 3. ከሆቴል ውጭ መስተንግዶ
- ሎት 4. የድንኳንና የወንበር ኪራይ
- ሎት 5. የደንብ ልብስ ሎት
- ሎት 6. የፅዳት እቃዎች
- ሎት. 7. የሆቴል መስተንግዶ
- ሎት 8. ዲጄ እና የሙዚቃ ኪራይ
- ሎት 9. ዲኮር ስራ ኪራይ
- ሎት 10. የደንብ ልብስ ማሰፊያ
- ሎት 11. የተለያዩ ህትመቶች
- ሎት 12. የመኪና ጥገና (ሰርቪስ)
ስለዚህ በዚህ የስራ ዘርፍ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤
- በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1. 30,000 ብር ሎት 2. 20,000 ብር ሎት 3. 20,000 ብር ሎት 4, 20,000 ብር ሎት 5. 20,000 ብር ሎት 6. 10,000 ብር ሎት 7, 30,000 ብር ሎት8. 15,000 ብር ሎት 9. 20,000 ብር ሎት 10. 5,000 ብር ሎት 11 20,000 ብር ሎት 12. 40,000 ብር የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀው ዝርዝር ጉዳዮችና የተጫራቾችን መመሪያ የያዘ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 150.00 /መቶ ሀምሳ ብር/ በመግዛት 9ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ፣
- ጨረታው መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀን ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 4 ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው የሚታሸግበት ቀን በ10ኛ ቀን 11፡30 ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቦታ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4
- ናሙና መቅረብ ባለባቸው እቃዎች ላይ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡ ህጋዊ ወኪል ለመሆናቸሁ የሚገልጽ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሣስባለን፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ እያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማህተብ ማድረግ አለበት፡፡ /VAT/ ያካተተ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መጥቀስ ይኖርበታል። ካልተጠቀሰ እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
- ኦርጅናል እና ኮፒውን ሰነድ ለየብቻ አድርጎ በማያያዝ ማስገባት ይኖርበታል፣
- በጨረታው ላይ የእቃውን ብዛት 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይቻላል
- በውሉ ላይ 25% መጨመር ይቻላል።
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በበጀት አመቱ ሙሉውን አመት የዋጋ ማስተካከያ የማናደርግ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡
ለበለጠመረጃ፡-
አድራሻ፡- አዲሱ ገበያ ኖክ ጀርባ የጉ/ክ/ከተማ አዲሱ ህንጻ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 04
በስልክ ቁጥር፡- 0921770036 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት
