ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት አመት ግልጋሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽሕፈት፣ የቧንቧ የኤሌክትሪክ የወርከ ሾፕ የጽዳት፤ የላብራቶሪ ኬሚካሎችና ባዮሎጂካል እንዲሁም ላብዌር መገልገያ፤ የላብራቶሪ ቋሚ እና የቢሮ፤ የICT ዕቃዎች በሎት በመከፋፈል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የተለያዩ ዕቃዎች ግዥ
የወጣ የጨረታ ማስታወቂ ቁጥር NVI 01/2018
ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት አመት ግልጋሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽሕፈት፣ የቧንቧ፣ የኤሌክትሪክ፣ የወርከ ሾፕ፣ የጽዳት፤ የላብራቶሪ ኬሚካሎችና ባዮሎጂካል እንዲሁም ላብዌር መገልገያ፤ የላብራቶሪ ቋሚ እና የቢሮ፤ የICT ዕቃዎች በሎት በመከፋፈል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡- ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የሚያሟሉ ሕጋዊ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና በመንግስት የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የቫት ከፋይ የምስክር ወረቀት ያላቸው ስለመሆናቸው ማረጋገጫ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ሠርተፍኬት፣ በጨረታው መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያው መጀመሪያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በየሎቱ በመክፈል ከኢንስቲትዩቱ ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተያያዘው ዋጋ ማቅረቢያ ፎርም መሰረት በመሙላት የድርጅታቸውን ማሕተምና ፊርማ በማድረግ፣ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ /CPO/ ወይም /ቢድ ቦንድ/ የጠቅላላውን 2% በማስያዝ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የኢንስቲትዩቱ ግዥ፤ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 10:30 ከሰኞ እስከ ዓርብ በሥራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 05 ቀን 2017 ዓ.ም በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ከጠዋቱ 4:00 ተዘግቶ 4:30 ይከፈታል፡፡ ጨረታው በተራ ቁጥር አምስት በተገለፀው መሰረት
- የጨረታ መከፈቻ ሰዓት በተመለከተ ነሐሴ 05 ቀን 2017 ሎት 1፣ 2፣ ከ4:30 እስከ 5:30 ሲሆን፣ሎት3 5፣ 6፣ 7፣ 8፣ ከ7:00 - እስከ 8:00 ሰዓት ሲሆን ነሐሴ 06 ቀን 2017 ሎት 4፣ 10፣ ከ4፡30 እስከ 5፡30 ሰዓት መሆኑን እናሳውቃለን፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋም ሆነ በሌላ የጨረታ ጉዳይ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ናሙናን በተመለከተ በዋጋ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ኢንስቲትየቱ በሚያሳየው ናሙና መሰረት ማቅረብ ይኖርበታል።
- አሸናፊ ተጫራች ዕቃዎቹን ለማቅረብ ውል ከፈረመና ተገቢውን የውል ማስከበሪያ 10% የመልካም ስራ አፈጻፀም ባስያዘ በ30 ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን ዕቃዎች በሙሉ በናሙናው መሠረት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በጨረታ የወጡ የተለያዩ መገልገያ ዕቃዎች እንዳስፈላጊነቱ 25% ሊቀንሱ ወይም ሊጨምሩ ይችላል።
- ንግድ ፍቃድ፤ቲን ነበር፤ ሲፒኦ የመሳሰሉት ከፋይናንሽያል ሰነድ ተለያይተው ለየብቻ በፖስታ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ቋሚ እቃን በተመለከተ ፋይናሽያልና ቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኮፒ እና አንድ ኦሪጅናል ተለያይተው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ቢሾፍቱ ከተማ ከመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ አለፍ ብሎ ከእንስሳት ሕክምና ፋኩልቲ አጠገብ፣
ለበለጠ መረጃ ለማግኘት
011-433-83-39 /09-12-22-98-61 መጠየቅ ይቻላል፡፡
ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት
