Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬሽን ከዚህ በታች የዘረዘሩትን ድርጅቱ ሲጠቀምባቸው የነበሩና የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬሽን ከዚህ በታች የዘረዘሩትን ድርጅቱ ሲጠቀምባቸው የነበሩና የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ለጨረታ የቀረቡ ንብረቶች የተለያዩ ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ የመኪና ባትሪዎች፣ ተቃጠለ የሞተር ዘይት

1.1 የንብረቱ ዝርዝር መረጃ

 

.

የዕቃው ዓይነት

መለኪያ

ብዛት

1

ያገለገሉ የተለያዩ አይነት የተሽከርካሪ ጎማዎች

በቁጥር

635

2

ያገለገሉ የተለያዩ የተሽከርካሪ ባትሪዎች

በቁጥር

97

3

የተቃጠለ የተሽከርካሪ ሞተር ዘይት

በበርሜል

28

 

  1. በጨረታው ላይ የሚወዳደር ማንኛውም ተጫራች (ግለሰብ ወይም ድርጅት) በዜግነት ኢትዮጵያዊ መሆን አለበት፡፡ ተጫራቹ ግለሰብ ከሆነ የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ማንነቱን የሚገልፅ የቀበሌ መታወቂያ ማቅረብ አለበት፡፡ ድርጅት ከሆነ ደግሞ የድርጅቱን የውክልና ደብዳቤ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  2. ተጫራቾች ሸጎሌ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ግዢ ዲፓርትመንት በመምጣት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለልስ 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ጠዋት 300-600 ከሰዓት730-1000 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ዘነበ ወርቅ በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ በመሄድ በአካል መመልከት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚገዙትን ከተራ ቁጥር 1 እስከ 3 ያሉትን ለእያንዳንዱ ያገለገሉ ዕቃ የጨረታ መነሻ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባን በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል። የንብርቶቹን የመነሻ ዋጋ አስር በመቶ (10%) ያልያስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
  5. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 20ኛው ቀን ከጠዋቱ 430 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 530 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ ይከፈታል። ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  6. የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። ዝርዝር መረጃውን በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል።
  7. አድራሻ፡- የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬሽን ጉለሌ ዕጽዋት ማዕከል አጠገብ

ለበለጠ መረጃ፡-

በስልክ ቁጥር 011-517-25-11 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬሽን

 

Save Tender