ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለተለያዩ ዲፓርትመንቶች የስልጠና ግብዓቶች፣ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች፣ የአይሲቲ ቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች፣ የተለያዩ መድሃኒቶች እና የክሊኒክ ቋሚ ዕቃዎች፣ የቢሮ መጋረጃ እና ምንጣፍ፣ የከብቶች መኖ ግዥ 1ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ በ2018 በጀት ዓመት ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ጀዊ/001/2018 ዓ.ም
ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለተለያዩ ዲፓርትመንቶች የስልጠና ግብዓቶች፣ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች፣ የአይሲቲ ቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች፣ የተለያዩ መድሃኒቶች እና የክሊኒክ ቋሚ ዕቃዎች፣ የቢሮ መጋረጃ እና ምንጣፍ፣ የከብቶች መኖ ግዥ 1ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ በ2018 በጀት ዓመት ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት
- ሎት 1 - የእንጨት ስራ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች፤
- ሎት 2 - የአውቶሞቲቭ አላቂ እና ቋሚ እቃዎች እና የመኪና ዕቃዎች፤
- ሎት 3 - የብረታ ብረት አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች፤
- ሎት 4 - የኮንስትራክሽን አላቂ እና ቋሚ እቃዎች፤
- ሎት 5 - የኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ አላቂ እና ቋሚ እቃዎች፤
- ሎት 6 - ቴክስታይል ሌዘር ጋርመንት የፉትዌር አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች፤
- ሎት 7 - የሆቴልና ሆስፒታሊቲ እና ጸጉርና ውበት አላቂ እቃ ቋሚ እቃዎች፤
- ሎት 8 - የፊዚኮ ኬሚካል የላብራቶሪ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች፤
- ሎት 9 - የከተማ ግብርና አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች፤
- ሎት 10 - የሰርቬይንግ የማሽነሪ ዕቃዎች፤
- ሎት 11 - የአይሲቲ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች፤
- ሎት 12 - የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች፤
- ሎት 13 - የከብቶች መኖ፤
- ሎት 14 - የቢሮ መጋረጃ እና ምንጣፍ፤
- ሎት 15 - የደንብ ልብስ ዕቃዎች፤
- ሎት 16 - የጽዳት ዕቃዎች፤
- ሎት 17 - የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች፣
- ሎት 18 - የተለያዩ መድሃኒቶች እና ለክሊኒክ የሚያስፈልጉ ዕቃዎች፤
ማንኛውም ተወዳዳሪ፡-
- በዚሁ ዘርፍ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፤
- የግብር ከፋይ TIN ሰርተፊኬት፤
- የቫት (VAT) ተመዝጋቢ፤
- በመንግስት ግዢ መሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢነት (Supplier list) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- በተጠየቀው ዝርዝር እስፔስፊኬሽንና መለኪያ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የሚያቀር ዋጋ 15% ቫት ማካተትና ዋጋም ሲሞሉ ኮሌጁ ባዘጋጀው ጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረተው እቃ ናሙና እንዲያቀርቡ በተጠየቀባቸው እቃዎች አስቀድሞ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የተጠየቀውን ናሙና ወይም ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው።
- ከላይ ለተገለፁት ሎቶች ከሎት 1 እስከ ሎት 9 ድረስ ለእያንዳንዱ ሎት 70,000 ብር (ሰባ ሺህ ብር) ብቻ CPO ማሰራት ሲሆን ከሎት 10 እስከ ሎት 12 ድረስ ለእያንዳንዱ ሎት 80,000 ብር (ሰማንያ ሺህ ብር) ብቻ ሲሆን ከሎት 13 እስከ ሎት 18 ድረስ ለእያንዳንዱ ሎት 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ብቻ ለሁሉም ሎቶች በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስም CPO በማሰራት ማስያዝ አለባቸው።
- ከላይ ለተዘረዘሩት ለእያንዳንዱ ሎቶች 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ግዢ ዳይሬክቶሬት ብሎክ 7 መጥተው መግዛትና መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን በ5/12/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ እስከ 16/12/2017 ዓ.ም ድረስ መግዛት ይችላሉ። በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሰነዱን ዋናውንና ኮፒውን በማሸግ ለዚሁ ጨረታ ተበሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በዚሁ ቀን ጨረታው በቀን 19/12/2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው እለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በግልፅ ይከፈታል። ከተጠቀሰው ሰዓት ውጪ ዘግይቶ የሚመጣ ተወዳዳሪ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን አሸንፎ ውል እስኪፈራረም ድረስ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ አይመለስለትም በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ተወዳድሮ ያሸነፈበትን እቃ ኮሌጁ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ በራሱ በትራንስፖርት ወጪ በማጓጓዝ ገቢ ማድረግ አለበት።
- አሸናፊው ተጫራች ውል ከመፈጸሙ በፊት ያሸነፈውን ዕቃ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
አድራሻ፡- ከመድኃኒዓለም መሰናዶ ት/ቤት ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ዊንጌት ቀለበት መንገድ ሳይደርሱ ወይም ጴጥሮስ ወጳሎስ ቤተ ከርስቲያን አጠገብ ነው።
ስልክ ቁጥር፡- 011-1-27-39-249
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
