በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምስ/ጎህ/ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ፡- ቋሚ እቃ፣ የፅህፈት መሳሪያ፤ የደንብ ልብስ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ አላቂ የህክምና ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የቧንቧ ዕቃዎችና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምስ/ጎህ/ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ፡- ቋሚ እቃ፣ የፅህፈት መሳሪያ፤ የደንብ ልብስ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ አላቂ የህክምና ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የቧንቧ ዕቃዎችና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የታደሰ የንግድ ፍቃድና የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለዚህም መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በመንግስት ንብረት ግዥ አስተዳደር ኤጀንሲ በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ (Tin) ቁጥር ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው እቃዎች ጥራትና ደረጃውን የጠበቀና ለዚህም ለእያንዳንዱ እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፍል የጨረታ ሰነዱን በት/ቤቱ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙበት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ በግልፅ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ) ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ጠዋት 4፡30 ሰዓት ላይ በት/ቤቱ በግ/ፋ/ን/አሰ/ቡድን ቢሮ ቀጥር 4 ይከፈታል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አዳራሻ፡- ካዛንችስ ቶታል ፊት ለፊት አዋሬ መንገድ ምስ/ጎህ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት
ስልክ ቁጥር 0115-15-56 ደውለው ይጠይቁ።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምስራቅ ጎህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
