Tender Detail

Tender Details

  • Company በደ/ምዕ/ኢት/ሕ/ከ/መንግስት የኮንታ ዞን
  • Address በደ/ምዕ :ኢትዮጲያ, Phone: 0917388691
  • Website
  • Deadline03 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • opening date2025-09-03 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Furniture , Cloth And Shoes

በደ/ምዕ/ኢት/ሕ/ከ/መንግስት የኮንታ ዞን በ2018 በጀት ዓመት ለሴ/መ/ቤቶች የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች በሎትı ፈርኒቸር፣ በሎት2 የደንብ ልብስ እና በሎት3 የጽዳት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ምዕ/ኢት/ሕ/ከ/መንግስት የኮንታ ዞን በ2018 በጀት ዓመት ለሴ/መ/ቤቶች የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች በሎትı ፈርኒቸር፣ በሎት2 የደንብ ልብስ እና በሎት3 የጽዳት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ለመጫረት የምትፈልጉ፤

1/ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ 2/ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ 3/ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር(TIN)፤ 4/ በመንግስት ግዥ ላይ የአቅራቢነት ሰርተፊኬት፣ 5/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና 6/ የመልካም ሥራ አፈፃፀም በየዘርፉ የ2016 ወይም 2017 ዓ.ም ኮፒ ማቅረብ የሚችል፤ በ2018 በጀት ዓመት ፈቃድ ያወጡትን የመልካም ሥራ አፈፃፀም አይመለከትም፡፡

7/ ተጫራቾች ለሎትı እና ለሎት2 የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ሲሆን በሎት3 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

8/ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ በ21ኛው ቀን ድረስ በኮንታ ዞን ፋ/መምሪያ የጨረታ ዶክመንት በመግዛት እና በዋጋ ማቅረቢያ በመሙላት ቴከኒካል 1፣ ፋይናንሻል ኦርጅናል 1 እና ፋይናንሻል ኮፒ 2 በድምሩ 4 ፖስታ የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ የጨረታ ፖስታ በማሸግ በኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

9/ በተራ ቁጥር 8 መሠረት የጨረታ ሣጥን የሚከፈተው ከላይ በተባለው በ22ኛው ቀን ሲሆን ይህ ቀን የመንግሥት ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡ዐዐ ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮንታ ዞን ፋ/መምሪያ ይከፈታል፡፡

10/ ተጫራቾች የጨረታ ዶከመንት የማይመለስ 400 (አራት መቶ ብር) በመከፈል ከኮንታ ዞን ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 9 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

11/ ተጫራቾች ጨረታውን አሸንፈው ውል በመግባት ንብረቱን እስከ ኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አመያ ከተማ ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡

12/ በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ላይ የተገለፁትን መስፈርቶችን የማያሟላ ተጫራች ለቴክኒካል ግምገማ አይቀርብም፡፡

13/ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0917388691/0917161785 ወይም 0910262925

አድራሻችን፡- በደ/ም/ኢ/ህ/ ከ/መንግስት ኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ከጅማ ከተማ በስተ ደቡብ 102 ኪ.ሜ በአመያ ከተማ ይገኛል፡፡

በደ/ምዕ/ኢት/ሕ/ክ/መንግስት የኮንታ

ዞን ፋይናንስ መምሪያ

Save Tender