Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
  • Address ሃያ ሁለት በሚወስደው መንገድ ለም ሆቴል አለፍ ብሎ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ህንፃ 7ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111562305
  • Website
  • Deadline27 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price150.00
  • opening date2025-08-27 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የቢሮ የፅዳት አገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ማሰራት ይፈልጋል።


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የቢሮ የፅዳት አገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ማሰራት ይፈልጋል።

የቢሮ የፅዳት አገልግሎት ግዥ

በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

  1. በዘርፉ የተሰማሩ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
  2. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበትና ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና በዚህ የተደራጁ እና ስለድርጅታቸው ሙሉ መረጃ የሚያሳይ/ፕሮፋይል እንዲሁም በዘርፉ መልካም የስራ ልምድ በማያያዝ ሰነዱ ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ 150.00 (አንድ መቶ ሀምሳ ብርበመክፈል ከመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የግዥ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 7ተኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 703 መግዛት ይችላሉ፣
  3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ቲኦቲ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. በጨረታ ላይ ያወጣናቸው እቃዎች በሙሉ ኦርጅናል እና ጥራቱን የጠበቀ ሆነው ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት /ቤት ድረስ ማምጣት አለባቸው፣ 
  6. ተጫራቾች ለገዙት ሰነድ ብቻ የሚወዳደሩበትን ዋጋ ቫት በመጨመር በሰም የታሸጉ ኤንቨሎፕ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የግዥ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 7ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 703 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ወይም በሚያቀርቡት እቃዎች ማቅረብ አለባቸው።
  8. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ሆነው ውል የተገባባቸውን እቃዎች በአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝና ከቢሮው የግዥ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የውል ስምምነት መፈጸም ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 300 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታው አከፋፈት ላይ ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 400 ሰዓት ይከፈታል።
  10. /ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

 

አድራሻ፡- ሃያ ሁለት መገናኛ ለም ሆቴል ኤልሳ ቆሎ አጠገብ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111 557 0595 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

 

Save Tender