የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል እቃዎች እና አገልግሎት በግዥ መለያ ቁጥር 01/2018 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል እቃዎች እና አገልግሎት በግዥ መለያ ቁጥር 01/2018 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ማሟሳት ያስባቸው መስፈርቶች፡-
1. በዘርፉ የተሰማራበት የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት (Tin) ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስና ቲኦቲ ተመዝጋቢ የሆኑበት ማስረጃ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና ማስረጃ ያላቸው፣
2. የጨረታ ማስከበሪያ CPO በባንክ የተረጋገጠ በየሎቱ ሎት-1 የፅህፈት መሳሪያ 40,000፣ ሎት-2 የደንብ ልብስ 30,000፣ ሎት-3 የጽዳት እቃዎች 40,000፣ ሎት-4 የህትመት-ስራዎች 2,000፣ ሎት-5 ለመፅሃፍትና አላቂ የትምህርት እቃዎች 1000፣ ሎት-6 የጓሮ አትከልት ዘር ግዥ 500፣ ሎት-7 የእንስሳት ህከምና አላቂ እቃዎችና መድሃኒቶች 500፣ ሎት-8 ትራንስፖርት አገልግሎት 5,000፣ ሎት-9 ለቢሮ መስተንግዶ 2,000፣ ሎት-10 እንጨት ነከ እድሳትና ጥገና-1,000፣ ሎት-11 ኤሌከትሮኒከስ እድሳትና ጥገና 1,000፣ ሎት-12 የመኪና እቃዎች 5,000፣ ሎት 13 የልብስ ስፌት 1,000፣ ሎት 14 የዲኮር ስራና ተያያዥ ስራዎች 500.00፣ ሎት 15 የጭነት /የጉልበት/አገልግሎት ከተደራጁበት መ/ቤት ደብዳቤ በማፃፍ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የወረዳ 10 ለፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል በባንከ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
3. ናሙና በተጠየቀባቸው እቃዎች ላይ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ናሙናው መግባት ይኖርበታል።
4. የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን ድረስ በዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በወረዳው አዳራሽ 4ኛ ፎቅ ይከፈታል።
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ዋጋውን ከቫት ጋር ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
6. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለም።
7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በየሎቱ 200/ሁለት መቶ ብር/በመከፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡
9. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ፦ ን/ስ/ላ/ከ/ከተማ ሳሪስ ኢካፍኮ 100 ሜትር ገባ ብሎ የወረዳ 10 አስተዳ ህንፃ ፋ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 15
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት
