Tender Detail

Tender Details


የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳዳር የፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥ የስራ ሂደት በ 2018 በጀት ዓመት በወረዳ ውስጥ ለሚገኙ ባለ በጀት መ/ቤቶች በበጀት ዓመቱ ለሚያከናውነው የእቃና አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም በሎት /ምድብ/ የግዥ አይነቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር /////4//የጨ/ 001/18

 

የኮልፌ ቀራንዮ ፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳዳር የፋይናንስ /ቤት የግዥ የስራ ሂደት 2018 በጀት ዓመት በወረዳ ውስጥ ለሚገኙ ባለ በጀት /ቤቶች በበጀት ዓመቱ ለሚያከናውነው የእ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም በሎት /ምድብ/ የግዥ አይነቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1 አላቂ የቢሮ እቃዎች (ስቴሽነሪ) ግዥ

ሎት 2 የጽዳት እቃዎች ግዥ

ሎት 3 የደንብ ልብስ ግዥ

ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ ግዥ

ሎት 6 የአትክልት እና የተለያዩ ዘር

ሎት 7 የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ

8 የመድረክ ዲኮር

ሎት 9 መስተንግዶ

ሎት 10 በወረዳው ውስጥ የሚሰሩ የተለያዩ ጉልበት ስራዎች

በመሆኑም /ቤታችን ከላይ ከተራ ቁጥር 1-10 በተዘረዘሩት የግዥ ምድቦች መወዳደርና መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች /አቅራቢ/ አወዳድሮ ግዥውን ለመፈፀም ይፈልጋል።

  1. የዘመኑ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ እና ተጫራቾች የተመዘገቡበትን ኮፒ ማቅረብ የሚችል
  4. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢዎች መሆን አለባቸው።
  5. የሚቀርበው የዋጋ ሰነድ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
  6. ጨረታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ ሎት1- 17,500 ሎት2- 13,500፣ሎት3- 16,880 ሎት4 16,852፣ሎት5- 9,777፣ሎት 6- 2,200 ሎት7- 12,000 ሎት8:- 2,500 ሎት9- 6,000 ፣ሎት10- 5,000 ለእያንዳንዱ ሎት በአድራሻችን CPO መቅረብ አለበት።
  7. በስራ ከህሎት የተደራጁ ኢንተርፕራይዝ ከሆነ በተደራጁበት ዘርፍ ላይ ብቻ ልዩ ድጋፍ የሚደረግላቸው ሲሆን ካደራጃቸው /ቤት ሀላፊ በተፈረመ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው ከስራ ዘርፍ ውጭ ለሆኑት እንደማንኛውም ነጋዴ የሚስተናገዱ ይሆናል።
  8. አሸናፊው ተጫራች በሰነዱ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል መዋዋል አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበውን ሰነድዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በየሎቱ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡።
  10. ከሎት 1-3 ለተገለጹት ዕቃዎች ሰነዱን በሚያስገቡበት ቀን ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ያላቀረበ ድርጅት ከውድድር ውጪ ይሆናል። በናሙናው ላይ ያለውን የጥራት ደረጃ ይዞ ካልተገኘ ተመላሽ ይደረጋል።
  11. ገዢው እካል የሚገዛውን እቃ እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
  12. ለአሸናፊ ተጫራ በሰነድ ውስጥ የተካተተውን ጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም እስከ 10 ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉበትን እቃ 10% ሲፒዮ አሰርተው ውል መዋዋል አለባቸው።
  13. ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን እቃዎች በወቅቱ ማቅረብ ካልቻሉ ያስያዙት ሲፒኦ ይወረሳል ተመላሽ አይደረግም/፡፡
  14. የእቃ ማስረከቢያ በኮ///ከተማ ወረዳ 04 የፋይናንስ /ቤት የግዥ/ንብረት አስተዳደር ይሆናል።
  15. በሚቀርበው የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ የድርጅቱ ሀላፊ ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው ከውክልናው ደብዳቤ አያይዞ ስምና ፊርማ የድርጅቱ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር መኖር አለበት።
  16. /ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ 6ወር ድረስ ውሉን ባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
  17. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ ለሚቆጠር 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና 11ኛው ቀን ጠዋት 400 ሰዓት ታሽጎ 430 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮ///ከተማ ወረዳ 04 የፋይናንስ /ቤት የግዥ ስራ ሂደት ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
  18. የዕቃ ማጓጓዣ ብር አሸናፊው ተጫራች ይሸፍናል።
  19. ጨረታው የሚከፈትበት 11ኛው ቀን የእረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በተከታዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  20. ተጫራቾች ሰነድ በሚያስገቡበት ጊዜ ከመስሪያ ቤቱ የተሸጠላቸውን ሰነድ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር መመለስ አለበት።
  21. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
  22. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- ከአየር ጤና ወደ አለም ባንክ በሚወስደው መንገድ ከትሮፒካል ከፍ ብሎ ወረዳ 4 ህንጻ 1 ፎቅ ፋይናንስ /ቤት

 

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር የፋይናንስ /ቤት

 

Save Tender