Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት(ኢኢግልድ) ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና ህትመቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡


ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የግዥ መስያ ቁጥር/ኢኢግልድ-001/2018

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት(ኢኢግልድ) ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና ህትመቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ሎት አንድ፡-የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች እና የፕሪተር ቀለሞች

ሎት ሁለት፡- የተለያዩ የዕዳት ዕቃዎች

ሎት ሶስት፡-የተለያዩ ደንብ ልብሶች

ሎት አራት፡ የህትመት አገልግሎቶች

ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዝርዝር የተመዘገበበት የምስከር ወረቀትና ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ እንዲሳተፍ የተፃፈለትን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል።

ለዚህ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ለሎት አንድ ብር የማይመለስ 400 (አራት መቶ ብቻ)፣ለሎት ሁለት ብር 300 (ሶስት መቶ ብቻ )፣ ለሎት ሶስት ብር 500 (አምስት መቶ ብቻ) እና ለሎት አራት ብር400 (አራት መቶ ብቻ) በመክፈል ከድርጅቱ ግዢ ቡድን በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ሎቶች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶች በተለያዩ ፖስታዎች በማድረግ_እንዲያቀርቡ እያሳሰብን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በማግስቱ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢኢግልድ ዋና መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን ከ11ኛው ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል።

ተጫራቾች በጨረታ ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለሎት አንድ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺ ብር ብቻ)፣ ለሎት ሁለት ብር 30,000 (ሰላሳ ሺ ብር ብቻ)፣ ለሎት ሶስት ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር ብቻ) እና ለሎት አራት ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር ብቻ) የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise) ስም በሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ከጨረታው ቴክኒካል ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡- በኢኢግልድ ዋና መ/ቤት ፒያሳ ከሊፋ ሕንፃ አካባቢ በስተሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ (የቀድሞ ጅንአድ) አራዳ ከ/ከተማ ወረዳ 2 ።

ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ :- በስልክ ቁጥር 0111-57-24-97 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ ይችላሉ፡፡

የኢትዮጲያ የኢንደስትሪ ግብዓቶች  ልማት ድርጅት

 

Save Tender