በጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በ2018 ዓ/ም በጀት አመት ለስራ አገልግሎት የሚውሉ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች ላይ ከታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሆነ አገልግሎቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በ2018 ዓ/ም በጀት አመት ለስራ አገልግሎት የሚውሉ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች ላይ ከታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሆነ አገልግሎቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡ በመሆኑም፡-
1. የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ማስወገድ የመኪና ከራይ፣
2. ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ማሽን የጥገና ባለሞያ፣
3. የደንብ ልብስ ስፌት፣
4. የእስረኛ ቀለብ፣
5. የትርጉም አገልግሎት ግዥ፣
6. ጎሚስታ፣
7. የደንብ ልብስ ግዥ፣
8. የፖሊስ ፓቶሮል መኪና መቀመጫ እና ብረት ከነሸራ ለማሰራት፣
9. የፖሊስ መዝናኛ ከበብ አገልግሎት ግዥ፣
10. የሚጫረቱበትን የዕቃ ዝርዝር የሚገልፅ ሰነድ የማይመለስ 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 በተከታታይ በስራ ቀን በጉ/ከ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፋይናንስ ግዥ አስተዳደር ከፍል ቢሮ ቁጥር 7 ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፤
11.የሚጫረቱበትን የዕቃ ዋጋ የሚገልጽ ሰነድ በታሽገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ እስከ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለዚያው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ አስገብቶ ይታሸጋል፡፡
12. ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑ ግብር ለመከፈላቸው ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡
13. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃዎች ናሙና ከጨረታ መክፈቻ ቀናት አስቀድመው ማቅረብ ለሚችሉባቸው ዕቃዎች አንዳንድ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
14. ተጫራቾች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም ከአ/አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት የቢሮ የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስከር ወርቀት አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
15. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ በየአንዳንዱ ሎት ማለትም ተራ ቁጥር 1 እስከ 9 ድረስ ያሉትን ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 3,000.00/ ሶስት ሺህ ብር / በባንክ የተረጋገጠ በC.P.O ብቻ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርበታል።
16. አሸናፊው አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ወዲያው ለአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና በC.P.O ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
17. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ማስታወቂያ በተጠናቀቀበት 10ኛው የስራ ቀን በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ በዚያው ዕለት ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል ። ቀኑ በስራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው በስራ ቀን 3፡30 ጨረታው ይከፈታል፡፡
18. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ ወይም መጠቀም አይቻልም።
19. መስሪያ ቤቱ በግዥ ወቅት 25% መጨመር መቀነስ ይቻላል።
20. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
21.ለበለጠ ለመረዳት በስልክ ቁጥሮች፡- 0111-56-64-07 /0111-57-91-50
09 20-29 88-66/09 32-45-10-64
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሲስ መምሪያ
