በሸገር ከተማ በገላን ከፍለ ከተማ የገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በገላን ወረዳ አስተዳደር ስር ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ፡- የቢሮ የፅህፈት መሳሪያዎችን የቢሮ ፈርኒቸርና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፣ የፅዳትና አላቂ የቢሮ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ገ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ጨረታ ቁጥር 001/2018
በሸገር ከተማ በገላን ከፍለ ከተማ የገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በገላን ወረዳ አስተዳደር ስር ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ፡- የቢሮ የፅህፈት መሳሪያዎችን የቢሮ ፈርኒቸርና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፣ የፅዳትና አላቂ የቢሮ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ስመሳተፍ-
-
በዘርፉ ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የግብር መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
-
በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዘጋቢ የሆኑ እና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
-
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ ለ15/ለአስራ አምስት/ የሰራ ቀናት ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር /በገላን ወረዳ ገቢዎች ጽ/ ቤት ሲንቄ ባንከ ቁጥር 1064793701213 በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋጋ በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው/አስራ ስድስተኛው የስራ ቀናት በገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከረፋዱ እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
-
ጨረታው በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከረፋዱ 4፡30 በገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት ተጫራቾች ባይገኙም _ ጨረታውን _ ከመከፈት አያግደውም፡፡
-
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚውል በባንክ በተረጋገጠ Cpo/ሲፒኦ/ ለቢሮ ጽሕፈት መሳሪያዎች 30,000/ሰላሳ ሺህ/ ለቢሮ ቋሚ ፈርኒቸር እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 50,000/ሀምሳ ሺህ/ ለቢሮ ፅዳት እና አላቂ እቃዎች 20,000/ሃያ ሺህ /ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
-
ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ዝርዝር መሰረት ሞልተው መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
-
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ፦ 0913321839/0910742350
በገላን ክፍለ ከተማ የገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
