የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2018 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ነገሮችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2018 የበጀት ዓመት:-
- Registrar System & Website development" ለአንደኛ ጊዜ ለማሰራት፣
- የተለያዩ የደንብ ልብሶች ለሁለተኛ ጊዜ ለማሰፋት፤
- *Fire Extinguisher /የእሳት ማጥፊያ ለሁለተኛ ጊዜ ለማስሞላት በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- 2017 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ በዘርፉ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባችሁን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ ሚችሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ኮፒና ኦሪጅናል ለየ ብቻ በተለያየ ፖስታ ማሸግ አለባቸው።
- ስርዝ ድልዝ ያለው፣ የማይታይ የጨረታ ሰንድ ወይም የዋጋ ዝርዝር ተቀባይት የለውም።
- ጨረታውን ካሸነፋ በኋላ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ዋጋ 10% ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኮሌጁ ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ክፍል ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ለእያንደንዱ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ አለባቸው።
- የ Registrar System & Website development" ጨረታው የሚከፈተው በ04/13/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የተለያዩ የደንብ ልብሶች ስፌት ጨረታው የሚከፈተው በ04/13/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:30 ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- "Fire Extinguisher/የእሳት ማጥፊያ” ጨረታው የሚከፈተው በ05/13/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉትን ዋጋ በመስሪያ ቤቱ ሰነድ ብቻ ላይ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታው ማስከበሪያ-
- "Registrar System & Website development" (20,000 ሃያ ሺህ ብር)
- የተለያዩ የደንብ ልብሶች ስፌት እና "Fire Extinguisher / የእሳት ማጥፊያ" 10,000 (አስር ሺህ ብር) በ"CBE, CBO, እና በSinge" ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0228123956 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ
