በምስራቅ ወለጋ ዞን የኪረሙ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ላሎት የመንግስት መ/ቤቶች ለ2018 የበጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል አላቂ ዕቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የሰራተኛ ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በምስራቅ ወለጋ ዞን የኪረሙ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ላሎት የመንግስት መ/ቤቶች ለ2018 የበጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል አላቂ ዕቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የሰራተኛ ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑ ግብር (2017-2018) የከፈሉ፤ በተጨማሪ እሴት ታክስ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና ቲን ቁጥር ያላቸው።
2. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ከ20/12/2017 እስከ 05/01/2018 ዒ.ም ድረስ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ/ ብር ኪረሙ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ክፍያ በመፈጸም የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ ከገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቀጥር 5 /አምስት/ መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ 10,000 /አስር ሽህ ብር/ በእያንዳንዱ የንግድ ዘርፍ ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ጨረታውን አሸንፈው ዕቃውን ለማቅረብ የውል ማስከበሪያ ዋጋ የአቅራቦቱ 10% የማስያዝ ግደታ አለባቸዋው።
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት ።
6. ተጫራቾች የዕቃውን ዋጋ ዝርዝር የተጠየቀውን (ስፔስፊኬሽን) ሳይለውጡ የጨረታ ማወዳደሪያ በቀረበው ሰነድ ላይ ዋጋው ከነተጨማሪ እሴት ታከስ /NAT/ በመሙላት፣ ስማቸውን ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማስፈርና ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶከመንታቸውን ኦሪጅናልና ኮፒ በተለያዩ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 05/01/2018 ዓ.ም ድረስ በቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው ሳጥን ጨረታው ከመዘጋቱ ከ11፡00 ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት በ06/01/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል። ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።
8. የጨረታው ሣጥን ከታሸገ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
9. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈባቸውን የዕቃ ዝርዝር ጥራታቸውንና ብዛታቸውን ጠብቆ ከውል ሰጭመ/ቤት በሚያደርገው የውል ስምምነት መሰረት ኪረሙ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሚገኘውየዉውል ሰጪ መ/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋል፡።
10. መ/ቤታችን በሚያወዳድረው ዕቃዎችን ብዛት ላይ እንደ አስፈላግነቱ 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ሰተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-09-20-40-90-64/ 09-26-36-47-74
በምስራቅ ወለጋ ዞን የኪረሙ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
