በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አጃምባ የመ/ደ/ት/ቤት በ2018 ዓ.ም የስራ ዘመን የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ሎትı. ቋሚ እቃ ኤሌከትሮኒክስ (6313) ሎት2 የደንብ ልብሶች (621) ሎት3. የጽህፈት መሳሪያና ሌሎች (6212) ሎት4. አላቂ የትምህርት እቃዎች (6215) ሎት5.የተለያዩ መሣሪያዎች እና መፃህፍት (6219) ሎት6.ሌሎች አላቂ እቃዎች (የፅዳት እቃዎች) (6218) ሎት7 ቋሚእቃዎች (6314) ሎት 8 የህክምና እና የላብራቶሪ እቃዎች (የቤተ-ሙከራ) (6214) ሎት9. የህትመት ስራዎች(6213) እንድትሳትፉ ይጋብዛል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂ
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አጃምባ የመ/ደ/ት/ቤት በ2018 ዓ.ም የስራ ዘመን የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ሎትı. ቋሚ እቃ ኤሌከትሮኒክስ (6313) ሎት2 የደንብ ልብሶች (621) ሎት3. የጽህፈት መሳሪያና ሌሎች (6212) ሎት4. አላቂ የትምህርት እቃዎች (6215) ሎት5.የተለያዩ መሣሪያዎች እና መፃህፍት (6219) ሎት6.ሌሎች አላቂ እቃዎች (የፅዳት እቃዎች) (6218) ሎት7 ቋሚእቃዎች (6314) ሎት 8 የህክምና እና የላብራቶሪ እቃዎች (የቤተ-ሙከራ) (6214) ሎት9. የህትመት ስራዎች(6213)
1.የጨረታው ቁጥር01/2018ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።
2.ተጫራቾች ለአቅርቦቱ አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ሰርተፍኬት እና የታከስ ከፋይነት ቲን ነምበር ሊኖራቸው ይገባል።
4.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ እያንዳንዱ ሎት200ብር በመክፈል ዘወትር በኮ/ቀ/ከ/ከ/ወ/ክ አጃምባ የመ/ደ/ት/ቤት ካራ ቆሬ ታክሲ ተራውን እንዳለፉ ወደ አጃምባ መውጫ ባለው መንገድ ብሎኬት ማምረቻው እንዳለፉ ባለውቅያስ ወደ ቀኝ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው በት/ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው በቢሮ ቁጥር 03 ፋይናስ ክፍል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 10 (አስር) የስራ ቀናት እሁድና ቅዳሜን ሳይጨምር ከጠዋቱ 2፤30 እስከ 11፡30 ምሳ ሰአትን ሳይጨምር ማግኘት ይችላሉ።
5. አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ መስጠት አይችልም፡፡
6.ገዢው ለሚገዛው ግዢ 20% ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል፡፡
7.ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን (ፋይናንሻል) እና ፎቶ ኮፒውን (ቴከኒካል ) ሰነዶች ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ (ቢሮ) ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአት ከo2፡30-ዘ፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8.ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተዘግቶ በዛው ቀን ከጠዋቱ 04፡30 ይከፈታል ፡፡
9.የሚቀርበው የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ የድርጅቱ ሀላፊ ስምና ፊርማ እንዲሁም አድራሻ እና ስልክ ቁጥር መኖር አለበት።
10.አሸናፊ ተጫራቾች በሰነዱ ውስጥ በተመለከተው ጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም እስከ7 ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% በሲፒኦ አስይዘው ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል።
11. መስሪያቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ 6 ወር ድረስ ውሉን ቢያድስ ምባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12.በጨረታ ሰነድ ላይ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮች ካሉ የማብራሪያ ጥያቄ በፅሁፍ ከጨረታው መከፈቻ 2ወይም 3 ቀናት በፊት ማቅረብ ይችላሉ ።
13.ተጫራቾች በጨረታው ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው በት/ቤቱ ግዢ ከፍል የስራ ሂደት ቅሬታውን በፅሁፍ ማቅረብ ይችላሉ በዚህ ከፍል የማይፈታ ከሆነ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ይችላሉ፡፡ የጨረታው ውጤት በተገለፀ 5ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ያላቀረበ ተጫራች በውጤቱ እንደተስማማ ተቆጥሮ ከአሸናፈው አካል ጋር ውል ይፈፅማል ።
14. አሸናፊው ድርጅት የግዢውን ውል ከፈረሙበት ቀን ጀምሮ ባሉ 10 የስራ ቀናት እቃውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
15. የጨረታውን አካሄድ ለማዛበትም ሆነ ለማጭበርበር የሚሞከር ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል።
16.ማንኛውም ተጫራች ለሚያስገባቸው ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
17. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 (11,500) ለሎት 2(8,800) ለሎት 3(8,900) ለሎት 4(6000) ለሎት 5(12,600) ለሎት 6(9,090) ለሎት 7(11,500) ለሎት 8(1,100) ለሎት 9(2000)
18. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
አድራሻ፡- በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/11 አጃምባ የመ/ደ/ት/ቤት ካራ ቆሬ ታክሲ ተራውን እንዳለፉ ወደ አጃምባ መውጫ ባለው መንገድ ብሎኬት ማምረቻው እንዳለፉ ባለው ቅያስ ወደ ቀኝ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው በት/ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው በቢሮ ቁጥር 03 ፋይናስ ክፍል።
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አጃምባ የመ/ደ/ት/ቤት
