Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወ 04 አራብሳ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ሎት 1. የቋሚ ንብረት፣ ሎት 2. ቋሚ አላቂ ንብረት፤ ሎት 3. የፅዳት እቃዎች፤ ሎት 4. የሰራተኛ ደንብ ልብስ፣ ሎት 5. የህትመት ስራዎች፤ ሎት 6. የህክምና መገልገያ መሳሪያ እና መድሀኒት፤ 7. የጥገና መሳሪያዎች እና ሎት 8. የደንብ ልብስ ስፌት ሎት 9. በቴከኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት/network infrastructure/፤ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2018

በአዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወ 04 አራብሳ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ሎት 1. የቋሚ ንብረት፣ ሎት 2. ቋሚ አላቂ ንብረት፤ ሎት 3. የፅዳት እቃዎች፤ ሎት 4. የሰራተኛ ደንብ ልብስ፣ ሎት 5. የህትመት ስራዎች፤ ሎት 6. የህክምና መገልገያ መሳሪያ እና መድሀኒት፤ 7. የጥገና መሳሪያዎች እና ሎት 8. የደንብ ልብስ ስፌት ሎት 9. በቴከኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት/network infrastructure/፤ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡

1. ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩበትን ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡

2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣

4. የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ C.P.O. ማቅረብ አለባቸው፡፡

የሎት ቁጥር

የእቃ ዝርዝር

 

ሎት 1

የቋሚ ንብረት

ብር 15,000.00

ሎት2

ቋሚ አላቂ ንብረት

ብር 8,000.00

ሎት3

የፅዳት እቃዎች

ብር 5,000.00

ሎት4

የሰራተኛ ደንብ ልብስ

ብር 5,000.00

ሎት5

የህትመት ስራዎች

ብር 5,000.00

ሎት6

የህክምና መገልገያ መሳሪያ እና መድሀኒት

ብር 15,000.00

ሎት7

የጥገና መሳሪያዎች እና የጥገና ስራዎች

ብር 4,000.00

ሎት8

የሰራተኛ የደንብ ልብስ ስፌት

ብር 4,000.00

ሎት9

በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት፤/network infrastructure/

ብር 15,000.00

 

 

6. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 405 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 303 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

8. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ C.P.O 10% ማስያዝ አለባቸው ፡፡

10. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፍኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡

11. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት ድርጅቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

12. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብት የተጠበቀ ነው፡፡

13. ለጥቃቂንና አነስተኛ ተጫራቾች የድጋፍ (የዋስትና) ደብዳቤ ከተሰጠበት አካል ደብዳቤው በፅፈት ቤቱ ኃላፊ የፀደቀ እና የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ ቲተር ያለው መሆን አለበት ፤ ከዛውጪ የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ከአያት አደባባይ አራብሳ ኮንዶሚኒየም በሚጭኑ ታከሲዎች ተሳፍረው ትምህርት ቤት ማዞሪያ የሚለው ቦታ ላይ በመውረድ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የስልክ ቁጥር:- +251-16-14-407

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 04 አራብሳ ጤና ጣቢያ

Save Tender