በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ በወረዳ 08 ውስጥ የሚገኘው ሙሴ አንደኛ ደረጃ/ት/ቤት ለ2018 ዓ/ም በጀት አመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ህጋዊ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018 ዓ/ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ በወረዳ 08 ውስጥ የሚገኘው ሙሴ አንደኛ ደረጃ/ት/ቤት ለ2018 ዓ/ም በጀት አመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ህጋዊ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች መሳተፍ ትችላላችሁ።
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ አላቂ የህክምና ዕቃዎች የተለያዩ የጥገና ስራዎች፣ ምርምርና የልማት ስራዎች እና ህትመት ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ እና በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ማቅረብ የሚችሉ
- ቲን ሰርተፍኬት /TIN/ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ከግብር ሰብሳቢው አካል የተሰጠ ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከት/ቤቱ ገንዘብ ቤት መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000 /አራት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸበት 7 የቅሬታ ቀናት በኋላ ባሉት 3 የስራ ቀናት ውስጥ ከት/ቤቱ ጋር ውል በመዋዋል በ5 ቀናት ውስጥ እቃውን በራሱ ወጪ በራሱ መኪና አጓጉዞ ማቅረብ አለበት፡፡
- የገዛችሁትን የጨረታ ሰነድ ምንም ሳይቀነስ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በሰም በታሸገ በሁለት ኤንቨሎፕ ታሽጎ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡ በመጨረሻው 10ኛው ቀን በ11:30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ድርጅት የውል ማስከበሪያ ዋስትና 10 /100/አስር ከመቶ/ ያሸነፈበትን እቃ ዋጋ በCPO በማስያዝ ከት/ቤቱ ጋር ውል ይፈርማል
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ሳሪስ በሚወስደው መንገድ ከንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፊት ለፊት ወደ ሃኪም ማሞ ቤት በሚወስደው መንገድ ጫፍ ላይ
ስልክ ቁጥር 0114 424694 /0114 70 7199
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ በወረዳ 08 ት/ጽ/ቤት
