ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ ለ2025/26 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡትን የሠራተኞች የደንብ ልብስ ህጋዊ እና በሙያው በቂ ልምድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
የሠራተኞች የደንብ ልብስ ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 08/2025/26
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ ለ2025/26 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡትን የሠራተኞች የደንብ ልብስ ህጋዊ እና በሙያው በቂ ልምድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የደንብ ልብሱ ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
|
1 |
የሙሉ ልብስ ጨርቅ |
በሜትር |
4,000 |
|
2 |
ሸሚዝ የወንድ |
በቁጥር |
1,908 |
|
3 |
ሸሚዝ የሴት |
በቁጥር |
460 |
|
4 |
ጫማ የወንድ |
በጥንድ |
954 |
|
5 |
ጫማ የሴት |
በጥንድ |
230 |
|
6 |
ከረቫት |
በቁጥር |
954 |
|
7 |
ካልሲ የወንድ |
በጥንድ |
1,908 |
|
8 |
ካልሲ የሴት |
በጥንድ |
460 |
ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን የጨረታ መመዘኛዎች የሚያሟላ ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች እንዲወዳደር ይጋብዛል።
- ተጫራቾች በዘርፉ በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው እንዲሁም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት እንዲሁም የዘመኑን ግብር ክፍያ ማረጋገጫ ሰነድ (Tax Clearance) ማቅረብ ይኖርባዋቸል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ግሎባል ባንክ አ.ማ. ስታዲየም ቅርንጫፍ በመክፈል እና የገቢ ደረሰኝ ይዘው በመቅረብ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ስታዲየም ከኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ ናሽናል ቢዝነስ ሴንተር 7ኛ ፎቅ ግዢና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ በመቅረብ ከመስከረም 07 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ስድስት ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሠላሳ ሺ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ. (CPO) ወይመ ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ዋጋ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ120 ቀናት ይሆናል። ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዋጋዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተቱ ሆነው ማንኛውም ወጪና የመንግስት ቀረጥ የተከፈለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
- ግልፅ ጨረታው መስከረም 07 ቀን 2018 ዓ.ም. ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ጠዋት 4፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መስሪያ ቤት ይከፈታል።
- ባንኩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ግዢና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ ስልክ ቁጥር 0115 581204 ወይም 0115 318097 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
