ብርሃን ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተገለጹትን ያገለገሉ አሉሚነየም፤ ብራታ ብረቶች እና መስታወት ለማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ያገለገለ አሉሚነየም፣ ብራታብረቶች እና የመስታወት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁ. ብ/ባ/ፕ/ማ - 01/18
ብርሃን ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተገለጹትን ያገለገሉ አሉሚነየም፤ ብራታ ብረቶች እና መስታወት ለማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
ለጨረታ የቀረቡ ያገለገሉ አሉሚነየም፣ ብራታብረቶች እና መስታወት ዝርዝር |
|
1 |
ያገለገሉ የተለያዩ አሉሚነየሞች |
|
2 |
ያገለገሉ አሉሚነየም - ፓኔሎች |
|
3 |
ያገለገሉ ብረታ ብረቶች |
|
4 |
ያገለገሉ መስታወቶች |
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ያገለገሉ አሉሚነየሞች፣ ብረታብረቶች እና መስታወቶች የጨረታ መነሻ ዋጋቸዉ እና የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን ለጨረታው በተዘጋጀው ሰነድ በዝርዝር ተቀምጧል።
- ያገለገሉ አሉሚነየሞች፣ ብረታብረቶች እና መስታወቶች ጎማ ቁጠባ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፊት ለፊት በሚገኘዉ የባንኩ ቅጥር ጊቢ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በማንኛውም የብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ ክፍያ ፈፅመው ደረሰኙን በማቅረብ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ቦሌ፣ ቀድሞ ብራስ ሆስፒታል ከነበረበት ቦታ ፊት ለፊት ከሚገኘው ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ፕሮፐርቲ እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ በመገኘት ለጨረታው የተዘጋጀቀወን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር በተገለፀው መሰረት ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ ያገለገለ ንብረት የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በC.P.O. ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በዝርዝር የተጠቀሱትን ያገለገሉ አሉሙንየሞችን፣ ብረታብረት እና መስታወቶች አጠቃለው ወይም በተናጠል መግዛት የሚችሉ ሲሆን ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ በመሙላት ከጨረታ ማስከበሪያ C.P.O ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ መስከረም 7 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት ቦሌ፣ ቀድሞ ብራስ ሆስፒታል ከነበረበት ቦታ ፊት ለፊት በሚገኘው ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ፕሮፐርቲ እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው መስከረም 7 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በፕሮፐርቲ እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ባይገኙ በሌሉበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸዉን ያገለገሉ አሉሙንየሞችን፣ ብረታብረት እና መስታወቶች ባቀረቡት ነጠላ ዋጋ መሰረት በአጠቃላይ ብዛቱ ተባዝቶ ጠቅላላ ዋጋውን በመክፈል አሸናፊነታቸዉ በተገለፀላቸዉ በአምስት ቀን ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህን ሳያደርጉ ቢቀር ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
- ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ሊሰርዝ ይችላል።
ተጨማሪ መረጃ ከፈልጉ በስልክ ቁጥር
0116631729 / 0116182624/ ደውለው ማግኘት ይችላሉ
ብርሃን ባንክ አ.ማ.
