የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ የደንብ ልብስ እና የአደጋ መከላከያ ቁሳቁሶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር OSE/NCB/007/2018
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ የደንብ ልብስ እና የአደጋ መከላከያ ቁሳቁሶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም አስፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገላጽን ተጫራቾች፡-
- የንግድ ምዝገባ ሰርትፍኬት
- የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No)
- የአቅራቢነት ማስረጃ (Supplier List)
- የሚፈለግባቸውን የመንግሥት ግብር ስለመወጣታቸው የሚገልጽ ማስረጃ፣ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን በመግዛት በ16ኛው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ ሰነዱን መግዛት የሚችሉት ከኢንተርፕራይዙ ዋና መ/ቤት ጎተራ አጎና ሠራዊት ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 402 ሲሆን የሁሉም ጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ የማይመለስ 200 ብር ሲሆን ሰነዱ የሚሰጠው በሶፍት ኮፒ ነው። ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 8:00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው እንዲትሳተፉ ተጋብዛችኋል።
የጨረታ ሳጥን በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንተርፕራይዙ ዋና መ/ቤት ጎተራ አጎና ሠራዊት ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ህንፃ /Baleker Tower/ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 603 ይከፈታል፡፡
ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ ማብራሪያ፡- ስ.ቁ 011-466-25-27/011-416-03-09 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ
