Tender Detail

Tender Details


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የእኖር ኤነር መገር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017/18 ዓ.ም በጀት አመት በእኖር ኤነር መገር ወረዳ የጥቅል ግዥ አላቂ እቃዎች (የፅፈት መሳሪያዎች)፣ጀነሬተሮች፣ ፈርኒቸሮች፣ የሚሊሻ ደንብ ልብስ እና የጽዳት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


                                               ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ 01

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የእኖር ኤነር መገር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017/18 ዓ.ም በጀት አመት በእኖር ኤነር መገር ወረዳ የጥቅል ግዥ አላቂ እቃዎች (የፅፈት መሳሪያዎች)፣ጀነሬተሮች፣ ፈርኒቸሮች፣ የሚሊሻ ደንብ ልብስ እና የጽዳት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ግለሰቦች/ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠየቀውን መስፈርት ማሟላት አለባችሁ፡፡ መስፈርት 

  1. በዘርፉ ፈቃድ ያለው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን 

  2. የዘመኑ ግብር/ታክስ የከፈለና ፈቃዱን ያደሰ መሆን አለበት 

  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ TIN Number ያለው ቫት ተመዝጋቢ የሆነ እና 

  4. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት በኦንላይን(Online) ሲስተም የተመዘገበ መሆን አለበት 

  5.  የጨረታ ማስከበሪያ የሚውል 1ዐ,ዐዐዐ/አስር ሺህ ብር/ከባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ የሚችል በሙሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ከእኖር ኤነር መገር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከግ/ን/አስተዳደር ስራ ሂደት ለአንዱ ሎት 500/አምስት መቶ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው ለተከታታይ ለ 15 የስራ ቀናት ብቻ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው ደግሞ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ሲሆን ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዋጋ ሞልተው አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ በማዘጋጀት በፖስታ በማሸግና በእናት ፖስታ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን የሚቀር መሆኑን እናሳስባለን፡አሸናፊ ድርጅቶች የሚቀርቡት እቃ ደረጃው የጠበቀ ቢሆን ወይም የጥራት ጉድለት ካለው መ/ቤቱ ተመላሽ የሚያደርግ ይሆናል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻ፡- እኖር ኤነር መገር ወረዳ ፋ/ኢ/ስ ጽ/ቤት 09-42-70-47-78/09-16-18-91-09

                                                   በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የእኖር ኤነር መገር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender