የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በ2018 በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የሽያጭና የአገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/ሽያጭና አገልግሎት/18 ዓ.ም
የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በ2018 በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የሽያጭና የአገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለመሸጥ ይፈልጋል፡-
1ኛ ለምግብነት የሚውል ንፁህ ስንዴ፣ ጤፍ፣ ገብስ፣ ቦሎቄ እና የእህል ሰብል ብጣሪዎች ሽያጭ
2ኛ የ2017/2018 ዓ/ም የሂሳብ ኦዲት አገልግሎት ጨረታ
3ኛ የትራንስፖርት ማጓጓዣ አገልግሎት ጨረታ
4ኛ ያገለገለ መኪና፣ የእርሻ ትራክተር ከነማረሻው የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ
በዚሁ መሠረት:
- ተጫራቾች በሥራ ዘርፉና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች ህጋዊ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውና የዘመኑን የመንግሥት ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታው ውድድር ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) በጨረታ ሰነድ ላይ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
- የጨረታው ሰነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 400.00 በመክፈል በሀዋሳ ከተማ በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ውስጥ በሰም በታሸገ ፖስታ /ኤንቨሎፕ/ በማድረግ ኦሪጂናልና ኮፒውን ለየብቻው ከተጓዳኝ ማስረጃዎች ጋር በማደራጀት በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ን/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በ15ኛው ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታው ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በወጣ በ15 ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጐ በእለቱ በ8፡30 ሰዓት በድርጅቱ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች በሚዘጋጀው የጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል።
- ስልክ ቁጥር 046 220 1752/2285/2117
የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት
