በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ሎቶች የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያዎች እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ህትመት ውጠቶች፣ የዕዳት እቃዎች፣ የቋሚ እና አላቂ የመረጃ ቴክኖሎጂ እቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሳሪያ መጽሀፍ ግዥ፣ለተሸከርካሪዎችና ሌሎች መጓጓዣዎች አድሳት ጥገናና ጌጣጌጥ ግዥ ፣ለፕላን፣ ለማሽነሪ እና ለተገጣሚዎች አድሳትና ጥገና፣ ህንፃና ቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳት እና ጥገና፣ የመስተንግዶ ግብአት (ቆሎና፣ ለህንፃ፣ ለቁሳቁስ ለተገጣጣሚዎች መግዣ (ቋሚ እቃዎች መግዣ) ልዩ ልዩ እቃዎች (አበባ እና አበባ ማስቀመጫ እንዲሁም ሌሎች ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር 01/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ሎቶች የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያዎች እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ህትመት ውጠቶች፣ የዕዳት እቃዎች፣ የቋሚ እና አላቂ የመረጃ ቴክኖሎጂ እቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሳሪያ መጽሀፍ ግዥ፣ለተሸከርካሪዎችና ሌሎች መጓጓዣዎች አድሳት ጥገናና ጌጣጌጥ ግዥ ፣ለፕላን፣ ለማሽነሪ እና ለተገጣሚዎች አድሳትና ጥገና፣ ህንፃና ቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳት እና ጥገና፣ የመስተንግዶ ግብአት (ቆሎና፣ ለህንፃ፣ ለቁሳቁስ ለተገጣጣሚዎች መግዣ (ቋሚ እቃዎች መግዣ) ልዩ ልዩ እቃዎች (አበባ እና አበባ ማስቀመጫ እንዲሁም ሌሎች ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጸውን መስፈርት የምታሟሉ አቅራቢዎች እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1. ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት (Tin) ያላቸው መሆኑን፤
3. ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር 9 ውስጥ የተመዘገቡ እና መረጃ ያላቸው፤
4. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምሥክር ወረቀት ከሰነዳቸው ጋር አያይዘው የሚያቀርቡ፤
5. የጨረታ ማስከበሪያ መጠን፡- የደንብ ልብስ ሎት አንድ 6,000.00፣ ለአላቂ የጽህፈት እቃዎች (ሎት2) ብር 12,000.00፣ ለህትመት ውጤቶች (ሎት3) ብር 12,700.00፣ ለጽዳት እቃዎች (ሎት4) ብር 3,000.00፣ ልዩ ልዩ የጽህፈት መሳሪያዎችና መጽሀፍት (ሎት5) ብር 5,000.00፣ ለተሽከርካሪዎችና ሌሎች መጓጓዣዎች እድሳት ጥገናና ጌጣጌጥ ግዥ (ሎት6) ብር 1,000.00፣ ለፕላን፣ ለማሽነሪ እና ለተገጣሚዎች እድሳትና ጥገና (ሎት7) ብር 1,200.00፣ ለህንጻ እና ለቁሳቁስ መገጣጠሚያዎች ዕቃ ግዥ (ሎት8) ብር 5000.00፣ የመስተንግዶ ግብአት (ቆሎና ውሃ) (ሎት9) ብር 7,000.00፣ ውሃ)፣ ፎቶ ኮፒና ፕሪንተር የጥገና ዕቃዎች ግዥ (ሎት10) ብር 10,000.00፣ ለህንፃ፣ ለቁሳቁስ ለተገጣጣሚዎች መግዣ (ቋሚ እቃዎች መግዣ) (ሎት11) ብር 5,000.00፣ ልዩ ልዩ እቃዎች (አበባና አበባ ማስቀመጫ እንዲሁም ሌሎች) (ሎት12) ብር 1,000.00 በባንክበተመሰከረለት (C.P.O) ብቻ መያዝ አለበት::
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ በእስታድየም አካባቢ ይሓ ሲቲ ሴንተር ሕንጻ 6ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የቅ/ጽ/ቤታችን የግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 607 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናሉንና ኮፒውን ለብቻ በማድረግ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ጋዜጣው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በ3፡00 ሰዓት ታሽጎ በ3፡ 30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅ/ጽ/ቤቱ 6ኛ ፎቅ ስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
8. የጨረታው መከፈቻው ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን 3፡ 00 ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፡፡
9. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን የዕቃው ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የውል ማስከበሪያ በባንከ በተመሰከረለት (CPO) በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል በመፈጸም አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች በሙሉ ቅ/ጽ/ቤቱ ንብረት ከፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
10. ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ የተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም በመጫረቻ ሰነዱ ላይ በተገለጸው የጨረታ ዋጋ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸላቸው በኋላ በተገለጸላቸው ቀን ቀርበው ውለታ ካልፈጸሙ እና የውል ማስረከቢያ ካልያስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
11. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተገለጸው መሰረት ለተጫረተበት እቃ ናሙና በድርጅቱ ማህተም ተረጋግጦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 5 58 25 56/0115 58 05 05 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
