የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ለ2018 የበጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ጎማዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የተጫራቾች መመሪያ
የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ለ2018 የበጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ጎማዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ አስፈላጊ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።
ስለሆነም ፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin number) ያላቸው፣
- ተጫራቾች የዕቃውን ዋጋ በሚሞሉበት ጊዜ የዕቃውን ዓይነት በግልፅ በቀረበው ስፔሲፊኬሽን መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
- ያቅራቢዎች ዝርዝር ላይ መመዝገባቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚያቀርበውን ዕቃ እስከ መ/ቤታችን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ ሙሉ ዶክሜንቶችን ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ከመ/ቤታችን ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ 9ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል የማይመለስ ብር 200 ብር መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ 9ኛ ፎቅ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳሪክቶሬት በተዘጋጀው ሳጥን መክተት አለባቸው።
- የጨረታው ሰነድ ስርዝ ድልዝ ከሆነ ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ- የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አዲስ አበባ ፍላሚንጎ በሚገኘው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መስተዳደር ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0115541816
የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ
