Tender Detail

Tender Details


በኮ/ቀ/ክ/ከ/ በወረዳ 07 ስር የሚገኘው ቤተል አንደኛና መካከለኛ ት/ቤት የተለያዩ ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ስራዎችን ማሰራት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018ዓ.ም

በኮ//// በወረዳ 07 ስር የሚገኘው ቤተል አንደኛና መካከለኛ /ቤት የተለያዩ ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች ማለትም: -

ሎት 1. የደንብ ልብስ፣ ሎት 2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ሎት 3. የህትመት ስራ ሎት፣ 4. የህከምና ዕቃዎች፣ ሎት 5. የፅህፈት ዕቃዎች፣ ሎት 6. የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 7. ለተለያዩ መሳሪያዎችና መጽሀፍ፣ ሎት 8, የማሸነሪ ጥገናዎች፣ ሎት 9. የተገጣጣሚዎች ዕድሳትና ጥገና፣ ሎት 10. መሰረተ ልማት፣ ሎት 11. ቋሚ የማሽነሪ እቃዎች፣ እና ሎት 12. ቋሚ የተገጣጣሚ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ስራዎችን ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል ፡፡

1. ከሎት 1-12 ለተጠቀሱት ዕቃዎች አግባብነት ያለውን ዋና የታደሰ የንግድ ፍቃድ የግብር መክፈያ ቁጥር ያላቸው እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣

2. የዘመኑን ግብር ከፍለው እንዲሁም በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝርለመመዝገባቸው የምስከር ወርቀት ማቅረብ አለባቸው።

3- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 230 እስከ 1130 በኮ//// በወረዳ 07 በቴል አንደኛና መካከለኛ ደረጃ /ቤት በመገኘት በየሎቱ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 1. 3,500(ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ) ሎት 2. 3.500 (ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ) ሎት 3. 10,00.00(አንድ ሺህ ብር ብቻ) ሎት 4. 1,500(አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ] ሎት 5 3,000.00(ሶስት ሺህ ብር ብቻ) ሎት 6. 3500(ሶስት ሺህ አምስት ብር ብቻ) ሎት 7. 1,500(አንድ ሺህ አምስት መቶ) ሎት 8. 1,500.00(አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ) ሎት 9. 2000.00(ሁለት ሺህ ብር ብቻ) ሎት 10.  3,500.00(ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ) ሎት 11. 3,500.00(ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ) ሎት 12. 3,500(ሶስት ሺህ አምስት መቶ) በባንክ የተረጋገጠ CPO ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በጋዜጣው ከወጣበት ቀን እስከ 10ኛው የስራ ቀን 230 እስከ 1130 ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች የሰነድን ኦሪጅናል እና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. ተጫራቾች የተጠቀሱትን እቃዎች እያንዳንዱ የሚሸጡበትን ዋጋ እና የጠቅላላውን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በመግለጽ በታሸገ ኤንቨሎፕ ገቢ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውን እና የጨረታ አይነት በመጥቀስ በቤተል አንደኛና መካከለኛ ደረጃ /ቤት ግዥ ከፍል ተዘጋጅቶ በተቀመጠው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

 

7. ተጫራቾች ለሚጫረቱት ዕቃ ናሙና ማቅረብ እና አሸናፊ ከሆኑ ደግሞ ውል ከመፈፀማቸው በፊት ቅድመ ብቃት (የዕቃ መጋዘናቸውን ለማሳየት ፈቃደኛ መሆን አለባቸው።

8. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃ በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።

9. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተረጋገጠ በኋላ የውል ማስከበሪያ CPO ማስያዝ አለባቸው፡፡

10. የሚሰሩ የጥገና ስራዎችን እና የሚፃፉ ፅሁፎችን በተመለከተ ተጫራቾች ቦታው ድረስ በመገኘት ማየት እና /ቤቱ በሚሰጠው ዝርዝር መሰረት እንደሚሰሩ አውቀው መሙላት አለባቸው፡፡

11. ተጫራቾች የሚያመጡት መረጃ በአማርኛ ቋንቋ የተተረጎመ መሆን አለበት፡፡

12. ማንኛውም ተጫራች ከተሰጠው እስፔስፊኬሽን ውጪ የፃፈ እና ስርዝ ድልዝ ያበዛ በጨረታው የማይሳተፍ መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡

13. አሸናፊ የሆነ ድርጅት 7 ቀናት በኃላ ውል መፈፀም የሚችሉ መሆኑን ማወቅ እንዳለባቸው እና ግዴታ እንደሆነ አዉቀዉ መሙላት አለባቸው፡፡

14. ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው ቀን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 400 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቤተል አንደኛና መካከለኛ ደረጃ /ቤት አዳራሽ ውስጥ የሚከፈት ይሆናል ፡፡

15. /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

16. ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃ የሚያስገቡት ዘወትር በስራ ሰዓት ጠዋቱ 230 እስከ 630 ከሰዓት 730 እስከ 1030 ሰዓት ይሆናል፡፡

17. ከት/ቤቱ የተሸጠውን ሙሉ የመደበኛ የጨረታ ሰነድ እና የጨረታ መመሪያን በአግባቡ በመሙላት ተመላሽ ማድረግ አለባችሁ፡፡

አድራሻ - ዓለም ባንከ ታክሲ ማዞሪያ ትውልድ ተስፋ /ቤት ፊት ለፊት

በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/07/ት/ጽ/ቤት/ቤተል አንደኛና መካከለኛ ደረጃ /ቤት

Save Tender