የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሚያከናውነው ምርጫ አገልግሎት የሚውል የምርጫ ቁሳቁስ ማሸጊያ ሰማያዊ ሳጥን ክዳን ግዥ ለመፈፀም ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የምርጫ ቁሳቁስ ማሸጊያ ሰማያዊ ሳጥን ክዳን ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር NEBE/NCB/04/2018
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሚያከናውነው ምርጫ አገልግሎት የሚውል የምርጫ ቁሳቁስ ማሸጊያ ሰማያዊ ሳጥን ክዳን ግዥ ለመፈፀም ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ባሉት የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ከቦርዱ ግዥ ስራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 107 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሠርተፊኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሠርተፍኬት እና በመንግስት ኤሌክትሮኒክስ ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ ስለመሆነ የሚያሳይማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተወዳዳሪዎች በሚወዳደሩበት መስከ ያላቸውን መልካም አፈጻጸም የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከቦርዱ የግዥ አስተዳደር የሥራ ከፍል በመውሰድ ሞልተው አግባብ ባለው አካል በመፈረም ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተወዳዳሪዎች ቴክኒካል ፕሮፖዛል እና ፋይናንሻል ፕሮፖዛል በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ጥቅምት 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ቦርዱ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
አድራሻችን፡- ቦሌ ፍላሚንጎ ካፌ ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- +251 115153468
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
