በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት በተያዘለት የመንግስት በጀት ለሆስፒታሉ መገልገያ የሚሆኑ የፅዳት አገልግሎት ዓመታዊ ውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግልጽ ጨረታ ቁጥር፡-04/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት በተያዘለት የመንግስት በጀት ለሆስፒታሉ መገልገያ የሚሆኑ የፅዳት አገልግሎት ዓመታዊ ውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታከስ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ ከገቢዎች በጨረታ እንዲሳተፉ የተገለፀበት ደብዳቤ ያላቸው እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ እና በዘርፉ የተሰማሩ የማይመለስ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ሰነድ በነፃ ለሚወስዱ ማህበራት በዘርፉ ስለመደራጀታቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
2.ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩ የእቃ ወይም አገልግሎት አይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የማይመለስ ብር300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሆስፒታሉ ፋይናንስ ዳይሬከቶሬት ቢሮ ድረስ በአካል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
3.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1. የፅዳት አገልግሎት ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺብር/ ዓመታዊ ውል በባንከ በተረጋገጠ CPO "ለጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል" ተብሎ በማዘጋጀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4.ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተዘጋጀው ዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ ብቻ በመሙላት የድርጅታቸውን ማጎተምና ፊርማ አኑረውፋይናንሻል ኮፒ 1 ቴክኒካል ኮፒ 1 ፋይናንሺያል ኦርጅናል 1 እና ቴከኒካል ኦርጅናል 1 በድምሩ 4 ፖስታ በማድረግ ዘወትር በስራ ቀንና ሰአት ከጠዋቱ 2፡30 – 11፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም ፡፡
5.ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ባይገኙ ጨረታው ከመከፈት አያግደውም፡፡ 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
6.ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል እንዲሁም ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
7.አሸናፊ ተጫራች አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች ያለምንም አቅርቦት ችግርአስተማማኝ የሆነ የእቃ ከምችት ያለውና የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10% ለውል ማስከበሪያነት አስይዞ ተገቢውን ውል በመፈጸም እቃዎቹን በሆስፒታሉ ግቢ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
8.ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፊል/የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ወይም ልዩ ስሙ ጥምቀተ ባህር ወይም
አቃቂ መሿለኪያ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጀ :- ስልክ 0924777840 በስራ ሰአት መደወል ይችላል ፡፡
የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል
