Tender Detail

Tender Details


የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ አይነት የፖሊስ ደንብ ልብስ (ፍራሽ፣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ)፣ ፅ/መሳሪያ፣ ፅ/ዕቃዎች፣ የመኪና ዕቃ መለዋወጫ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና የህክምና መገልገያ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የተለያዩ አይነት ዕቃዎች ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ ማስታወቂያ ቁጥር፡- (አንድ) 01/2018 .

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን 2018 በጀት ዓመት የተለያዩ አይነት የፖሊስ ደንብ ልብስ (ፍራሽ፣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ) /መሳሪያ፣ /ዕቃዎች፣ የመኪና ዕቃ መለዋወጫ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና የህክምና መገልገያ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  • የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
  • በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  • የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  • የታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀትና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ሰርተፊኬት ያላቸው
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  • የትብብር / ማቅረብ የሚችሉ፤
  1. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ ለሚያቀርቡት የዕቃ ዋጋ የተሞላው ዋጋ
  • የተሞላው ዋጋ ከብር 50,001.00 እስከ 500,000.00 ከሆነ የብር 5,000.00 በባንክ የተመሠከረለት ቼክ /CPO/ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • የተሞላው ዋጋ ከብር 500,001.00 እስከ 1,000,000.00 ከሆነ የብር 10,000.00 በባንክ የተመሠከረለት ቼክ /CPO/ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • የተሞላው ዋጋ ከብር 1,000,001.00 እስከ 5,000,000.00 ከሆነ የብር 50,000.00 በባንክ የተመሠከረለት ቼክ /CPO/ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • የተሞላው ዋጋ ከብር 5.000,001.00 በላይ ከሆነ የብር 100,000.00 በባንክ የተመሠከረለት ቼክ /CPO/ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  1. ተጫራቾች አንድ ተጫራች የሰጠውን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው:: የተሞላው ዋጋ ከዘጠና ቀናት (90) በታች መሆን የለበትም፡፡
  2. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የቴክኒካል ስፔስፊኬሽን እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በቅጂ ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል 15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 1100 ሰዓት ድረስ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ግዥና ፋይ//አስተደደር ዳይሬክቶሬት በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በጨረታ ሰነድ ላይ በተጠቀሰው መሠረት በግልጽ ማቅረብ አለባቸው።
  6. ጨረታ የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ቀን በኋላ በቀጣዩ የሥራ ቀን እስከ 0600 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታውም በዚሁ ዕለት ከሰዓት በኋላ 0800 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሚሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  7. ኮሚሽኑ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል በሚዋዋልበት ጊዜ 20% የመጨመር ወይንም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ኮሚሽኑ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል ከተዋዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስት ወርባለው ጊዜ ውስጥ 25% የመጨመር መብት አለው፡፡
  9. ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ሞባይል ቁጥር 09-10-06-29-54 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን

 

Save Tender