የጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ሴክተር መ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት 1- ኤሌክትሮኒከስ 2- ጽ/መሣሪያ 3- ፈርኒቸር 4- ሞተር ሳይክል 5- አላቂ የጽዳት ዕቃዎች 6- የስፖርት ትጥቆችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ሴክተር መ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት 1- ኤሌክትሮኒከስ 2- ጽ/መሣሪያ 3- ፈርኒቸር 4- ሞተር ሳይክል 5- አላቂ የጽዳት ዕቃዎች 6- የስፖርት ትጥቆችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. የዘመኑ የግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርያላቸው፣
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
4. በአቅራቢነት የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
6. ተጫራቾች ዝርዝር የመጫረቻ ሰነድ ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት እስከ 15 ባሉት ቀናት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 መውሰድ ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በእያንዳንዱ ሎት ብር 70,000 /ሰባ ሺህ ብር/በባንከ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በማዘጋጀት በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ የሚወዳደሩበትን ዓይነት በፖስታው ላይ በመለየት በግዥና/ን/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን እስከ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን በ3፡30 ታሽጎ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል፡፡
10. የጨረታ መከፈቻ በበዓላት ወይም በሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይሰዓት ይሆናል።
11. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመቅረብ ወይም በስልከ ቁጥር0468813338/0468810275 በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ/ክ/መንግስት የጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
