Tender Detail

Tender Details

  • Company Fire and Disaster Risk Management Commission (በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን)
  • Address አዲስ አበባ ቅ/ጊዮርጊስ ፊት ለፊት በሚገኝ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን 1ኛ ፎቅ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 41 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-878-76-86
  • Websitehttps://edrmc.gov.et/
  • Deadline27 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price50.00
  • opening date2025-10-27 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Printing And Publishing , Water Pipes And Fittings , Stationery Materials

በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የካ ቅርጫፍ ጽ/ቤት በ2018 በጀት የአንደኛ ዙር ግልፅ ጨረታ፣ ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችን ፣ ሎት 2 ህትመት ሎት 3. የጽዳት ዕቃዎች እና ሎት 4 ለቧንቧ እና አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።


ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የካ ቅርጫፍ ጽ/ቤት በ2018 በጀት የአንደኛ ዙር ግልፅ ጨረታ፣ ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችን ፣ ሎት 2 ህትመት ሎት 3. የጽዳት ዕቃዎች እና ሎት 4 ለቧንቧ እና አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሟሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

 

1. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ ፡፡

2. በመስኩ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልጽ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ የተሰጠ ማስረጃ እና የግብር መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች ከወሰዱት የጨረታ ሰነድ ዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ውጪ በሌላ ሞልቶ ቢያቀርቡ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

5.ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 50.00/ሃምሣ ብር ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት እሰከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው፤ በ11ኛው ቀን እስከ አራት ሰዓት ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው እለት ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፉ አዳራሽ ውስጥ የሚከፈት ሲሆን ዘኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።

8. በጨረታው ለመሳተፍ ከሎት 1 - 4 ላለው ለእያንዳንዱ ሎት 2,000/ሁለት ሺ ብር/ የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው ፡፡

9. ዘግይተው የቀረቡ የመወዳደሪያ ሠነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡

10, ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ የሚሆኑ ሲሆን ወደፊትም በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡

11. በጨረታው ተወዳድሮ ያሸነፈውን እቃ በቅርንጫፉ ጥራት /ቴከኒከ/ኮሚቴው ጥራቱ ሲረጋገጥ ተጫራቹ በራሱ ትራንስፖርት ጭኖ በቅርንጫፉ ንብረት ክፍል ማድረግ ይኖርበታል ፡፡

12. ተጫራቾች ለጨረታው ያቀረቡት ዋጋ የሚቆይበት ጊዜ ቢያንስ ለ60 ቀናት መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል ፡፡

13, ቅርንጫፉ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ የሚገዛውን እቃ ወይም አገልግሎት ብዛት /መጠን እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 20 በመቶ ለመቀነስ ወይም ለመጨመር መብት ይኖረዋል፡፡

14. በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የካ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

 

15. ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ ወይም መረጃ ማግኘት ሲፈልጉ በስልክ ቁጥር 0116-68-47-97 /0116-66-81-73 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 አድራሻ ፡- ከመአድን ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ ዮድ አቢሲኒያ ኢተርናሽናል ሆቴል አጠገብ

የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የካ ቅርጫፍ ጽ/ቤት

Save Tender