Tender Detail

Tender Details


ኢትስዊች አ.ማ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ ላፕቶፕ እና ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ስዎች፣ የአልሙኒየም፣ የመስታወት፣ የብረታ-ብረት ቁርጥራጮች፣ የባነር ሸራዎች፣ ቶነሮች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የኔትወርክና የኤሌክትሪክ ገመዶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


 

ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ኢትስዊች አ. በሁሉም የሃገራችን ባንኮችና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለቤትነት የተመሰረተ ተቋም ሲሆን በቅርቡ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትም እየተቀላቀሉት ይገኛል የተቋቋመበት አላማም በፋይናንስ ተቋማት መካከል ተናባቢነት (Interoperability) ለመፍጠር እና የሃገር ውስጥ የክፍያ ስርዓት (Domestic payment scheme) ለማልማት እና ለሁሉም የፋይናንስ ተቋማት የሚያገለግል የጋራ መሰረተ ልማት (Shared Infrastructure/Platforms) ለመስጠት ነው።

ኩባንያችን የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ ላፕቶፕ እና ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ስዎች፣ የአልሙኒየም፣ የመስታወት፣ የብረታ-ብረት ቁርጥራጮች፣ የባነር ሸራዎች፣ ቶነሮች የፅዳት ዕቃዎች፣ የኔትወርክና የኤሌክትሪክ ገመዶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት የዘመኑን ግብር የከፈለና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው ወይም ግለሰብ ከሆነ የታደሰ መታወቂያ ወይም ማንነታቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውን እና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጥቅምት 3 ቀን 2018 . ጀምሮ እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2018 . ድረስ በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 200 እስከ 1100 እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 200 እስከ 600 ካዛንቺስ አካባቢ ከእናት ባንክ //ቤት ጎን በሚገኘው የኢትስዊች ህንፃ 2 ፎቆ የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል በመገኘት ዕቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ ማየት ይችላሉ
  2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ለዕቃዎቹ የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት ከመቶ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል
  3. ተጫራቾች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ ዕቃዎች የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ኢትስዊች አ. ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2018 . ዓት 800 (ስምንት) ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል ዘግይቶ የደረሰ ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይሆናል
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነዱን ባስገቡበት አድራሻ ጥቅምት 11 ቀን 2018 . ዓት 830 (ስምንት ሰዓት ከሠላሳ) ይከፈታል
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት አይኖረውም
  6. የጨረታው አሸናፊዎች ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 2 (ሁለት) ተከታታይ ቀናት ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከፍለው ሙሉ በሙሉ ማንሣት ይኖርባቸዋል ይህ ሳይሆን ቢቀር ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ለኩባንያው ገቢ ይሆናል
  7. በጨረታው የወደቁ ተሳታፊዎች ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ወዲያው የሚመለስላቸው ሲሆን፣ ለአሸናፊ ተጫራቾች ግን ከሚገዟቸው ዕቃዎች ክፍያ በኋላ ተመላሽ ይሆናል
  8. ኩባንያችን የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ

+251-11-557-12-04/05

 

ኢትስዊች ..

 

Save Tender