Tender Detail

Tender Details


ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም የእቃዎቹ ዝርዝር ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ ሎት 2 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ ሎት 4 የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና ሎት 5 የቧንቧ, ዕቃዎች ሲሆኑ ዝርዝሩንና ብዛቱን በጨረታ ሰነዱ ላይ ተጠቅሷል፡፡


የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም የእቃዎቹ ዝርዝር ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ ሎት 2 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ ሎት 4 የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና ሎት 5 የቧንቧ, ዕቃዎች ሲሆኑ ዝርዝሩንና ብዛቱን በጨረታ ሰነዱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

በዚህ መሠረት ድርጅቱ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ሰመግዛት ስለሚፈሰግ ተጫራቾች፡-

1. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 /ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ከድርጅቱ መግዛት ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ/ በመከፈል ከፋይናንስ ከፍል ቢሮ ቁጥር 07 መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራች የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና የቫት መመዝገቢያ ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

4. የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀው የብር መጠን በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል።

5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ሞልቶ በሚያቀርበው ዋጋ የእያንዳንዱ እቃዎች ብራንዳቸውን፣ ዓይነታቸውንና ሌሎች የዕቃው መግለጫዎች በጨረታ ሰነዱ መሰረት መግለጽ ይኖርበታል፡፡

6. ተጫራች ከዚህ ቀደም በተለያዩ ድርጅቶች የጨረታ አሸናፊ በመሆን በተሳተፉባቸው የመልካም የሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

7. ተጫራቶች ለመወዳደር በሎት የተግለፁት በመረጡት ለእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርበታል።

8. በጨረታው መሰረት ተጫራቹ አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች አሸናፊ መሆኑን ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በሙሉ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ መሰረት በራሱ መጓጓዣ ስቴድየም ወደ ሚገኘው ይሓ ሲቲ ሴንተር ህንጻ የይሓ ሪል እስቴት ንብረት ክፍል /11ኛ ፎቅ ድረስ በማጓጓዝ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡

9. ለአሸናፊው ድርጅት/ግለሰብ የዕቃዎቹን ዋጋ የሚከፈለው ዕቃዎቹን ሙሉ በሙሉ ካስረከበ በኋላ ይሆናል፡፡

10. ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 8 /በስምንተኛው የሥራ ቀን/ በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይሆናል፡፡

11. ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8 /በስምንተኛው የሥራ ቀን/ በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይሆናል፡፡

12. ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ መገኘት ይችላል፡፡

አድራሻ-አዲስ አበባ ስቴድየም ቤተ ዛታ ሆስፒታል ፊት ለፊት —ይሓ ሲቲ ሴንተር“ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ስልክ ቁጥር- የቢሮ 0115580129/03/0115576954/ ሞባይል 0922079575 /0911417904 ደውለው ይጠይቁ።

ማሳሰቢያ:- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር

Save Tender