Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service (EPSS) (የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት)
  • Address አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከጳውሎስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-2765-294
  • Websitehttps://epss.gov.et/
  • Deadline29 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2025-10-29 00:00:00
  • Categories Other Sales , Vehicle , Vehicle tire , Used Items

የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ንብረትነታቸው የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፤ አይስፖክ፤ ካርቶኖች፤ ጎማዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች ባሉበት ሁኔታና ቦታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር መአኤ/02/2017

 

የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ንብረትነታቸው የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፤ አይስፖክ፤ ካርቶኖች፤ ጎማዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች ባሉበት ሁኔታና ቦታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በሟሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ውስጥ በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ/ ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 ስከ 10:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ዕቃዎቹን ከላይ በተጠቀሰው ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ
  4. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል፡፡ የዕቃዎቹ የመነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) ያላስያዘ እና በሠንዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።
  5. ጨረታው ጥቅምት 19 ቀን 2018 . ከቀኑ 800 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 8:15 ሰዓት ተጫራ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት መዝናኛ በብ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
  6. በጨረታው አሸናፈ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው 4 የሰራ ቀናት በኋላ ባሉት 3 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ ፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
  7. የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ባወጣው ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ዕቃዎቹን 5 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው
  9. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-2765-294 ወይም 011-2783-008 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  10. የመድኃኒት ቅራቢ አገልግሎት ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት

 

Save Tender