በአብከመ የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የቢሮ መገልገያ የፅህፈት መሳሪዎች፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ ደንብ ልብስ፣ የውሃ ጉድጓድ ቆፋሮና መስመር ዝርጋታ እና የህትመት ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብከመ የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የቢሮ መገልገያ የፅህፈት መሳሪዎች፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ ደንብ ልብስ፣ የውሃ ጉድጓድ ቆፋሮና መስመር ዝርጋታ እና የህትመት ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ-
1.በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው በበጀት ዓመቱ (2018) ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤ ለስራው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ /TIN/ያላቸው፡፡
2.የጨረታው ሰነድ ከከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 50 በግዥ/ፋ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች _ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮ.ብር 300/ሶስት መቶ ብር ብቻ /በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
3.ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናና ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ ከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስራ ስድስተኛው/16/ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
4.ጨረታው በአስራ ስድስተኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
5.ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ2%/ከሁለት ፐርሰንት/በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንከ ትእዛዝ/CPO/ማስያዝ አለባቸው፡፡
6.የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይድምር ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
7.መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
8.የዕቃው ርከከብ ቦታ በከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ይሆናል፡፡
9.ውድድሩ በነጠላ ዋጋ የምንወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
10.ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል በግንባር በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 0913131148 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡
የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል
